አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2/2015 ዓ.ም፡- መከላከያ ሠራዊት “በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጉራባች ወረዳዎች በጥፋት ሃይሎች ታግቶ የቆየ” 7250 ኩንታል እሕል በቀጠናው የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ባደረገው ዘመቻ በማሥለቀቅ ለባለንብረቶች ገቢ አደረኩ።
“ሻለቃ አማከል ባልቻ እንደገለፁት ከራሱ በፊት ሀገሩንና ሕዝቡን ያሚያስቀድመው ስራዊታችን በቀጠናው በነበሩ ሕገወጥ ሃይሎች የኢ-መደበኛ እንቅስቃሴ በበርሃ ታግቶ የነበረውን አህል በ104 የጭነት መኪና በመጫን ወደ ጃዊ ወረዳ ፈንደቃ ከተማ ማድረስ ችሏል” ሲል የመከላከያ ሠራዊት በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣዉ መረጃ ገልጿል።
የህንኑ የግል ንብረት ከጥፋት ሃይሎች አስለቅቆ ለባለንብረቶች ለመመለስ በተደረገው እንቅስቃሴ የህብረተሠቡ የተቀናጀ ትብብር እና ጥቆማ የሚደነቅ መሆኑን የገለፁት ሻለቃ አማከለ በአካባቢው የሚገኙ የሜካናይዝድ እና እግረኛ ክፍለጦሮች ከሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ጋር ተቀናጅተው በመስራት የተገኘ ውጤት መሆኑንም አብራርተዋል።
“የመከላከያ ሰራዊቱ ብርቱ ጥረት እና የአካባቢው ነዋሪ ተቀራርቦ በመስራቱ በድብቅ ተከማችቶ የነበረው እህል ለባለ ንብረቶቹ የደረሠ ሲሆን በባለ ንብረቶች አማካኝነት ለገበያ እንዲውል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የጃዊ ወረዳ ሰላም እና ፀጥታ ሃላፊው ንጉስ ይፍሩ ተናግረዋል” ሲልም መረጃው ጨምሮ ገልጿል።
የጃዊ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደስታ አንለይ በበኩላቸው የመካለከያ ሠራዊት በአስቸጋሪ መልክዓ ምድር በመሰማራት ሃገርን እና ህዝብን የሚያኮራ ተግባር በወረዳው ባሉ አካባቢወች በማከናወን ላይ መሆኑን ገልፀዋል።