ዜና፡ መንግስት በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እና ሃይማኖት አባቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ማዋከቦች፣ እስሮች እና ግድያዎችን  በአስቸኳይ እንዲያስቆም ኢዜማ አሰሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2/ 2015 ዓ.ም፡- መንግስት በኦሮሚያ ክልል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እና በሃይማኖት አባቶች ላይ እየደረሰ ያለው ማዋከቦች፣ እስሮች እና ግድያዎችን በአስቸኳይ ኢንዲያስቆም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አሳሰበ።  

ኢዜማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር መሰረት በማድረግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በተቋሙ የተፈጠረውን ውስጣዊ ችግር ተከትሎ የመንግስት ኃላፊዎች ያደረጓቸው ንግግሮች ሁኔታውን ለተወሳሰበ ችግር ዳርገውታል ሲል ሀሳቡን አንፀባርቋል።

ፓርቲው ከመንግስት ሃላፊዎች አባባሽ ንግግሮች ባሻገር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የጸጥታ ኃይሉ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት በተግባር ካሳዩት ወገንተኝነት እና አድሎ በከፋ መልኩ ፈፅሞ የጸጥታ ስጋት ባልሆኑ ምእመናን ላይ ጭካኔ የተሞላበት የኃይል እርምጃ በመውሰዳቸው የንጹሐን ዜጎች ሕይወት እንዲቀጠፍ እና አካል እንዲጎድል ምክንያት ሆኗል ብሏል፡፡

አሁንም የሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ መንግሥት እጁን መክተቱ መዘዙ ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

“በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ የንጹሐን ዜጎችን ሞት፣ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና መፈናቀሎችን ተቆጣጥሮ ሰላምና ደኅንነትን ማስከበር ያልቻለው የክልሉ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገባ ችግሩን የከፋ እንዲሆን አድርጓል” ሲል የክልሉን መንግስት ከሷል፡፡ ቀጥሎም የፌደራል መንግሥቱም ቢሆን ይህን ዐይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት በገሀድ እያየ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ምንም ዓይነት እርምጃ ባለመውሰዱ ዋነኛው ተጠያቂ ያደርገዋል ሲል አክሏል፡፡

የእምነቱ ተከታዮች የሃይማኖት ተቋማቸውን ትዕዛዝ በማክበር ጥቁር በመልበሳቸው ምክንያት በፀጥታ አካላት በየመንገዱ እና በቤተ እምነታቸው ቅጥር ግቢ መደብደብ፣ ማዋከብ፣ ማሠር እና ማስፈራራት ደርሶባቸዋል ያለው ኢዜማ “ይኽ የዜጎችን ነፃነት መጋፋት በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ተግባር” ሲል ድርጊቱን ኮንኖታል። በአስቸኳይ እንዲቆምም አሳስቧል፡፡

በዛሬ እለት እንኳን በወሊሶ መስመር በወለቴ፣ አለምገና እና ሰበታ ቀውሱ ተባብሶ ቀጥሏል ያለው የድርጅቱ መግለጫ  ግልፅ በሆነ መንገድ ጣልቃ እየገባ ያለው መንግሥት ለሀገር ሰላምና ደህንነት ስጋት እየፈጠረ መሆኑን ተገንዝቦ ኃላፊነቱ ህግን አክብሮ ማስከበር መሆኑን በመረዳት እንዲንቀሳቀስ አሳስቧል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.