ዜና፡ ለተጎጂዎች የሚቀርብ እርዳታ የወንጀለኞች መጠቀሚያ መሆኑ የሚያሳዝን ነው ሲሉ ሴናተር ጂም ሪሽ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3/2015 ዓ.ም፡- አለም በከፍተኛ ደረጃ የምግብ እጥረት ባጋጠማት ሰዓት ለተጎጂዎች የሚቀርብ እርዳታ የወንጀለኞች መጠቀሚያ መሆኑ የሚያሳዝን ነው ሲሉ የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል የሆኑት ሴናተር ጂም ሪሽ ገለጹ። ሴናተር ጂም ሪክ ይፋ ያደረጉት መልዕክት እንደሚያመለክተው የአሜሪካን መንግስት በኢትዮጵያ የሚገኙ ተጎጂዎችን ለመታደግ ያበረከተው እርዳታ በወንጀለኞች በተደራጀ እና በተጠና መልኩ ቁሳዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሲሉ መዘረፉ እጅግ ያሳዝናል ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ተግባር ሁሉንም ግብር ከፋይ አሜሪካዊ ሊያስቆጣ ይገባል ያሉት ሴናተሩ ከሁሉም ቀዳሚ የሆነው የተሳካ የውጭ እርዳታ መርህን የባይደን አስተዳደር በሚያሳዝን ሁኔታ ሊያስጠብቅ አልቻለም ሲሉ ተችተዋል። የአሜሪካ የእርዳታ ኤጀንሲዎች የተጠመዱት የበርካቶችን ህይወት የቀሰፈው ጦርነት መቆሙ ላይ እና የእርዳታ እህል ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች አቅርቦቱ እየተሻሻለ መጥቷል የሚለው ነው ያሉት ሴናተር ጂም ሪሽ አሁን ግልጽ የሆነው ነገር በዋሽንግተን፣ ኒውዮርክ እና ሮም የሚገኙ የእርዳታ ተቋማት መሪዎች የአሜሪካ ህዝብ እርዳታ ለታለመለት አላማ መዋሉን ሊያረጋግጡልእ እንዳልቻሉ ነው ሲሉ ተችተዋል። ስርቆቱ እየተከናወነ ያለው አለም በከፍተኛ ደረጃ የምግብ እጥረት ባጋጠመበት ወቅት መሆኑ በቁስል ላይ ተጨማሪ ቁስል እንደመፍጠር ነው፤ ተቀባይነት የለው ሲሉ አምርረው ገልጸዋል።

የእርዳታ አቅርቦቱ ላልታለመለት አላማ መዋሉ የኢትዮጵያ መንግስት ባህሪ አመላካች ነው ሲሉ የወቀሱት ሴናተሩ የኢትዮጵያ መንግስት ከእኛ ጋር በሙሉ እምነት፣ በመተማመን እየሰራ ነው ብሎ መገመት ሞኝነት ነው ሲሉ ገልጸዋል፤ በድጋሚ አንታለልም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በትላንትናው እለት ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ሴኔት የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሚካኤል ማኮል በሰጡት አስተያየት በኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና ሰውሰራሽ ምክንያት የተረጂዎች ቁጥር በጨመረበት ወቅት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ የሚያካሂደውን የእርዳታ አቅርቦት ማቋረጡ አሳዘኝ ነው ብለዋል። የአሜሪካ መንግስት እና ህዝብ ለጋስነት ገደብ የለሽ ተደርጎ ግን መቆጠር የለበትም ሲሉ አሳስበው ምርመራ እንዲካሄድ፣ አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ  እና የኢትዮጵያ መንግስት የእርዳታ አቅርቦቱ በፍጥነት እንዲጀመር ትብብር እና እምነት ማግኛ እንቅስቃሴዎች ማድረግ እንደሚጠበቅበት አመላክተዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.