ዜና፡ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ የሙካራ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ነሐሴ 23፤ 2014 ዓ.ም፣አዲስ አበባ፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ የሙከራ ስራውን መጀመሩን አስታወቀ። ደንበኞች በ07 የሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የፈልጉትን ስልክ ቁጥር መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉ አስታውቋል።

ኩባንያው በድሬዳዋ በጀመረው የሙከራ ትግበራ የ2G፣ 3G እና 4G ኔትዎርኮችን ማስጀመሩን የገለፀ ሲሆን የተቋሙ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ደንበኞች ሲም ካርድ እና የስልክ ቀፎ መግዛት ይችላሉ ብሏል።

ሲም ካርዶቹ የደንበኛነት ማስጀመሪያ  የድምፅ፣ እና የፅሁፍ ጥቅል አገልግሎት እንዳላቸው የተገለፀ ሲሆን የጥቅል አገልግሎቱ  ሲያልቅ በተመሳሳይ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሽያጭ ማዕከላት እና መደብሮች መግዛት እንደሚቻል አስታውቋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አክሎም በዚሁ ከተማ የሙከራ ኔትወርክ ድንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የፅሁፍ መልዕክቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ ብሏል።

በተጨማሪም የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ የሚረዳ ‘700’ አጭር ቁጥር የደንበኞች አገልግሎት የጥሪ መስመር ድርጅቱ ያቀረበ ሲሆን በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሶማልኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻልም ድርጅቱ አስታውቋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.