እለታዊ ዜና፡ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11/ 2015 ዓ.ም፡- በሲዳማ ብሔር ዘንድ የራሱ የሆነ የቀን አቆጣጠር ቀመር ወይም ስርዓት ያለው በጨረቃና በስነ-ከዋክብት የሚመራ በአያንቱዎች (በአዋቂዎች) ተለይቶ ለጎሳ መሪዎች (ገሮ) ተገልፆ በጪሜሳዎች (በሀገር ሽማግሌዎች) ይፋ ተደርጎ በየዓመቱ የሚከበረው የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምበላላ በዓል በዛሬው እለት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

ይህ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገው በዓል ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት የመሽጋገራችን ብስራት እውን መሆን ማሳያ መሆኑን ተገልጧል፡፡

በዚህ በዓል ክቡር ከሆነው የሰው ልጅ እኩል ለእንስሳትና ለእፅዋት ልዩ ክብር የሚሰጥበት፣ ከብቶች የማይታረዱበት እፅዋት የማይቀጠፉበት ይልቁንም እንክብካቤ የሚደረግበት ልዩ ቀን መሆኑን የሃዋሳ ከተማ ኮሙኑኬሽን ገልጧል፡፡

የሲዳማ አባቶች ከበዓሉ አስቀድመው የተጣላን ለማስታረቅ፣ መጪው አዲስ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የብልፅግናና የደስታ እንዲሆን በፆም ፀሎት ፈጣሪን ለመለማመን የያዙት ፆም የሚፈታበትም ነው።

በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በፌደራል ደረጃ እስከ ክልል እና ወጣቶች እየሰሩ መሆናቸውን ተገልጧል፡፡

የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት መልዕክት ፍቼ ጫንባላላ የአዲስ ዘመን ብስራት ነዉ፤ የሲዳማ አባቶች (አያንቶች) በከዋክብትና በጨረቃ ዉደት የዘመን ቀመር በማበጀት አሮጌዉን ዓመት ሸኝተዉ፣ አዲሱን አመት በፍሰሃና በተድላ እንድንቀበል ያበጁልን ታላቅ የአስትሮኖሚያዊ እዉቀት የሚገለጥበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.