
በጌታሁን ፀጋዬ
አዲስ አበባ:ጳጉሜ 2/2013-“በኢትዩጱያ ባለፉት ሳምንታት በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች የሚሞቱና ፅኑ ህሙማን ቁጥር በጣም መጨመረ ነው ሲሉ ” የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናገሩ ፡፡
ሚኒስቴሯ አዲሱ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ እንደሆነ ገልጣ ማህበረሰቡ ክትባቱን በየጤና ተቋማቱ በመገኘት እንዲወስድ እንዲሁም የኮቪድ ፕሮቶኮልን ሁሉም ተቋማትና ግለሰቦች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
በኢትዩጱያ ባለፈው ሳምንት ብቻ8ሺህ 300 ሰዎች በወረርሽኙ ሲያዙ እስካሁን በአገሪቱ 313ሺህ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል፡፡ ከ4ሺ 700 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኑ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል፡፡
በኮቪድ ወረርሽኝ የመያዝ ምጣኔውም ከ1በመቶ ወደ 20 በመቶ አሻቅቧል ባለፈው ሳምንት 118ሰዎች ሞተዋል፡፡AS