ትንታኔ፡- ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በቁሳቁስ አቅርቦት አጥረት ምክንያት “ሙሉ ለሙሉ” አገልግሎት መስጠት የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ ዶክተሮች አሳሰቡ፤ በሆስፒታሉ የሞት ቁጥርም ከአስር በመቶ በላይ አሻቅቧል

ከአይደር ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ክፍሎች አን ። ፎቶ፡ ትግራይ ቲቪ

በአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጠኞች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21/2015 ዓ.ም፡- የትግራይ ክልል ትልቁና ዋነኛው ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ድጋፍ ካልተደረገለት “ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል” ሲሉ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ክብሮም ገ/ስላሴ አስጠንቅቀዋል።

ዶ/ር ክብሮም ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር በኢሜል ባደረጉት ልዩ ቃለ ምልልስ “ሆስፒታሉ ሙሉ ለሙሉ ስራውን አቁሞ እናዳይዘጋ አየታገልን አንገኛለን፡፡ የምንቆጥበው አንኳን ሳይኖረን ባለን ሀብትና አቅም የምንችለውን ያህል እየታገልን ነው” ብለዋል። አክለውም “በእርግጥ ከበባው በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ካልተነሳ ማን በህይወት ይቆያል?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ባለስልጣናት አርብ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል ውስጥ አንደ ክትባትና አንቲባዮቲክ የመሳሰሉ መድኃኒቶች በከፍተኛ ሁኔታ አያሽቆለቆለ ነው ማለታቸውን እና ካሉት የጤና ተቋማት 9 በመቶ የሚሆኑ ብቻ አገልግሎት አየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ዶቼ ቨሌ ዘግቧል።

ዩኒሴፍ ቅዳሜ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት “ከነሓሴ አስከ መስከረም ባለው ጊዜ ውስጥ የመጀመርያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ አገልግሎት የሚያገኙ ህፃናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች አንዲሁም የሚያጠቡ አናቶች ቁጥር 84 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ” ብሏል።

በፌዴራል መንግስትና በትግራይ ክልል ሃይሎች መካከል ለሁለት አመታት በዘለቀው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

በጦርነቱ ሳቢያ ሆስፒታሎችና ሌሎች የህዝብ መገልገያዎች የወደሙ ሲሆን አጅግ አስፈላጊ የሆኑ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችና የመድኃኒት አርዳታዎች ተስተጓጉሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ህጻናትን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አስፈላጊ የህክምና አንዲሁም የአንክብካቤ አገልግሎት ለማጣት ተገደዋል።

በመላው ትግራይ የሚገኙ ሆስፒታሎች አስፈላጊ የሆነ የመድኃኒት አቅርቦት ባለመኖሩ ሰዎች በቀላሉ ታክመው ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች እየሞቱ መሆኑን ዶክተሮች ይናገራሉ።

በቅርቡ በተላለፈው ቢቢሲ አፍሪካ ዓይ ዶኩመንተሪ ፕሮግራም ላይ በትግራይ ክልል በዓብይ – ዓዲ ሆስፒታል በምግብ አጥረት የ19ኝ ወር ህጻን ልጅ የተጎዳባት ወላጅ አናቱ ወደ ህክም ይዛው ስትሄድ ያሳያል፡፡ በሆስፒታሉ ውስጥ ለህፃኑ ክትትል የሚያደርግለት ዶክተር የተመጣጠን ወይም አልሚ ምግብ በሆስፒታሉ ውስጥ አንደሌለ ጠቅሶ ምንም ሊያደርግለት አንደማይችል ሲገልጽ ይታያል። “ወተት አየሰጠነው አይደለም ምክንያቱ የለንም፤ አማራጭ ሰለሌለ ኦክጅን ነው አየሰጠነው ያለው” ይላል ህጻኑን በቅርበት የሚከታተለው ዶክተር።

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በፌደራል መንግስት ይተዳደር የነበረው የትግራይ ክልል ትልቁ ዓይደር ሆስፒታል ውስጥ ነገሮች አየከፉ መሆኑ ነው የተነገረው።

አንደ ዶ/ር ክብሮም ገለጻ ፋርማሲዎች አስፈላጊ መድኃኒቶች አልቆባቸዋል፣ የኬሚካል ማዋሀጃ (ሬጀንት) ባለመኖሩ አንዲሁም አዲስ አበባ ብቻ የሚጠገኑ መሳሪያዎች በመበላሸታቸው እና አንዳንዱ ደግሞ ኢንተርኔት የሚፈልጉ በመሆናቸው እንዲሁም አንድ ኤምአርአይ የመሳሰሉት የህክምና መሳሪያዎች የኤሌክትሪክ ኃይል የሚሹ በመሆኑ የራዲዮሎጂ ክፍል አገልግሎት ሊቋረጥ ችሏል።

ሆስፒታሉ አስፈላጊ የህክምና ግብአቶችን ስላለገኘ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት አቋርጧል ያሉት ዶ/ር ክብሮም “ በኩላሊት በሽታ የተጠቁ ህሙማን አጣ ፈንታ ሞት ነው” ብለዋል።

የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር (ICRC) መድኃኒቶች በመለገስ እና በማጓጓዝ ለሆስፒታሉ ይረዳ እንደ ነበር፤ ነገር ግን ወደ ትግራይ የየብስ ትራንስፖርት አንዲሁም የአየር በረራ ከተከለለ ጊዜ ጀምሮ እርዳታ ማድረግ እንዳልቻል ዶ/ር ክብሮም ገልጸዋል።

አለም አቀፍ የስኳር ህመምተኞች ፌዴሬሽን አና የኢትዯጵያ ስኳር ህምመተኞች ማህበር የስኳር (የኢንሱሊን) አና ሌሎች የዲኤም መድሃኒቶች ለሆስፒታሉ ሲልኩ የነበረ ሲሆን “ መንግስት ግን አግጓቸዋል” ይላሉ ዶክተሩ።

“በቤታቸው ሄደው አንዲሞቱ ነው የምንልካቸው” በማከልም “የካንሰር በሸታ አጅግ አስፈሪ ሆኗል ” ይላሉ ዶ/ር ክብሮም፡፡ በሆስፒታሉ የሚገኙ ሃኪሞች፤ ታማሚዎች የካነሰር በሽታ ተጠቂ መሆናቸው ለመግለጽ አጅግ አየተሰቃዩ ነው የሚሉት ዶክተሩ ምክንያቱን ሲያስረዱም፤ ለቀዶ ጥገናም ሆነ በካንሰር የተጠቃ ታማሚ የሚወሰደው መድኃኒት (ኬሞቴራፒ) በሆስፒታሉ ስለሌለ ነው ብለዋል። “የምርመራ ውጤት ነግረን፤ በቤታቸው አንዲሞቱ አንልካቸዋለን” ብለዋል ዶ/ር ክብሮም፡፡

እድሜያቸው በ56 የሚገመት አንድ አናት ስር የሰደደ የሆድ ካንሰር የነበረባቸው ሲሆን በህክምና በመሳሪያ እና መድኃኒት አጥረት ምክንያት ቀዶ ጥገና ማድረግ ባለመቻሉ ታማሚዋ ወደ ቤታቸው አንዲመለሱ ተደርጓል ሲሉ በዓይደር ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ሃኪም ዶክተር ፋሲካ ዓምደ ስላሴ ለአዲስ ስታንዳር ገልጸዋል። “በቀዶ ጥገና መሳሪያ አጥረት ምክንያት ለሁለት ወራት ያህል የካንሰር ቀዶ ጥገና ሕክምና አቁመናል” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

በተከታታይ የፀረ-ኤች አይቪ መድኃኒት ይወስዱ የነበሩ ሰዎችም መድኃኒታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል ያሉት ዶክተሮቱ አሁን የሚታዩ የመድኃኒት አቅርቦት መቆራረጥ ጋር ተያይዞ የሚመጣው ተፅእኖ ለሚቀጥሉት አመታት ሊቆይ ይችላል ብለዋል። በሆስፒታሉ አንቲባዮቲክ ባለመኖሩ ዶክተሮች ማንኛውንም የአንቲባዮቲክ መድኃኒት ለመጠቀም የተገደዱ ሲሆን “አሁን በቀጥታ ከሚሞተው ባሻገር መድኃኒት መጠባበቅ ብቸኛ አማራጫችን አንዳይሆን እንሰጋለን” ሲሉ ገልጸዋል።

ከሆስፒታሉ የተገኘ መረጃ አንደሚያመላክተው ለረጅም ጊዜ የሆስፒታሉ የሞት መጠን ከ2 በመቶ በታች ሲሆን የጽኑ ህሙማን (አይ ሲ ዩ) ሞት መጠን ከ5 በመቶ በታች ነበረ። ጦርነት ከተነሳ በኋላ ግን አጠቃላይ በሆስፒታሉ የሞት መጠን ወደ ከ10 በመቶ በላይ ከፍ ያለ ሲሆን የፅኑ ህሙማን (አይ ሲ ዩ) ሞት መጠን 29 በመቶ ሊደርስ ይችላል።

“በቤት ውስጥ የሚሞቱ የታኪሚዎች ቁጥር ግምት ውስጥ መግባት አለበት ምክንያቱም ሁኔታቸው ተስፋ ቢስ ከሆነ ወደ ቤታቸው አንልካቸዋለን፤ አንዳንዳ ቤተሰቦች የእሬሳ ማጓጓዣ ዋጋ ውድ ሰለሚሆንባቸው ታማሚዎቹ በህይወት እያሉ ነው ወደ ቤት የሚወስድዋቸው” ብለዋል ዶ/ር ክብሮም።

ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በአመት ውስጥ ከ300ሺ በላይ የሚሆኑ ታማሚዎች ሲያስተናግድ የቆየ ሲሆን በትግራይ ክልል ውስጥ በተደረጉ ቀዶ ጥገና ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነውን ዓይደር ሆስፒታል አከናውኗል። ከጦርነቱ በኋላ የሆስፒታሉ አጠቃላይ ታካሚዎችን የመቀበል መጠን ወደ 200ሺ ዝቅ ብሏ

፡፡ በተጨማሪም በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ሆስፒታሎች የመድኃኒት አጥረት ስላለባቸው፣ በጦርነት ምክንያት ስለወደሙ ወደ ዓይደር ሆስፒታል የሚመጡ ተማሚዎች ቁጥር ቢጨምርም ሆስፒታሉ ግን የተፈለገውን ያኅል ማስተናገድ አልቻለም፡፡

ዓይደር ሆስፒታል በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ብቸኛ ድንገተኛ ቀዶ ጥገና ህክምና የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡በቀዶ ጥገና ቁሳቁስ አጥረት ምክንያት ካንሰርን ጨምሮ ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታ የተጠቁ ታማሚዎች ወደቤታቸው አንዲመለሱ አየተደረጉ ነው ብለዋል ዶ/ር ክብሮም።

“የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የእጅ ጓንት አጥበን ድጋሜ አንጠቀምበታለን”

ዶ/ር ክብሮም እንዳሉት ወደ ሆስፒታል ለሚመጡ ህሙማን በቅድሚያ የሚያስፈልጉ መድኃኒቶች፤ የህጻናት ክትባቶች፣ አንቲ-ራቢስ መድሀኒቶች፣ አንቲ ቬነም፣ ኢንሱሊን፣ የዲያሊሲስ ሪጀንቶች፣ የካንሰር ኬሞቴራፒ፣ አንቲባዮቲክስ እና አይ ቪ ፍሉድና የመሳሰሉት ናቸው።

ሆስፒታሉ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መደኃኒቶች ከአንድ አመት በላይ ሲጠቀም ቆይቷል፤ ካለ ማደንዘዣም ቀዶ ጥገና አያደረገም ይገኛል ይህም “በዚ ዘመን ያልተሰማ” ነው ብልዋል ዶ/ር ክብሮም።

“የቀዶ ጥገና ጓንቶችን አጥበን በድጋሜ አንጠቀማለን፤ ቁስሎችን ለመንከባከብ የፕላስቲክ ከረጢቶችን አንደ ጓንት አንጠቀማለን፤ የገበታ ጨው ውሃ ውስጥ በማቅለጥ አንደ ጨዋማ ነገር አንጠቀምበታለን፤ የጥጥ ቀሚሶቹ አንደ ሻሽ አንጠቀምበታለን” በማለት ዶ/ር ክብሮም ስላለው አስከፊ ሁኔታ አስረድተዋል። “በዚህ መንገድ የበርካታ ወጣቶችን እና የእናቶችን ህይወት መትረፍ ችለናል” ሲሊም አክለዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ሆስፒታሉ ለኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ለኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር አስቸካይ የህይወት አድን መድኃኒት አቅርቦት አንዲደረግለት ደብዳቤ መጻፉ ይታወቃል።

ሆስፒታሉ በትግራይ ክልል ውስጥ 26,768 የሚሆኑ የስኳር ህመምተኞች እንዳሉ ገልጾ ከነዚህም ውስጥ 16,420ዎቹ የደረጃ አንድ ሙሉ በሙሉ የኢንሱሊን ጥገኛ ሲሆኑ 8,224 የሚሆኑት ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው ብሏል።

ዶ/ር ክብሮም እንዳሉት የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከግንቦት 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ደመወዝ አልተከፈላቸውም። “የትርፍ ሰአት ክፍያን ጨምሮ ደመወዝ አይከፈለንም፡፡ ሰራተኞች ከዚህ በፊት በባንክ ውስጥ ያጠራቀሙት ብርና ሃብትን አንኳ መጠቀም አልቻሉም” ብለዋል። “በብርታትና ጽናት ህዝባቸው አያገለገሉ ይገኛሉ፤በሚችሉት አቅም የታማሚዎች ህይወትን ለማዳን ሳምንቱን ሙሉ ቀንና ለሊት አየሰሩ ነው” ሲሉ አክልዋል።

“በትግራይ ምንም አይነት የጤና አገልግሎት የለም ይህንንም አለም ማወቅ አለበት፤ ህዝቡ ሙሉ ለሙሉ በዝምታ ሊሞት ነው፤ ዓለም ይህንን ያውቃል ግን በዝምታ ማየትን መርጥዋል” ብልዋል ዶ/ር ክብሮም።

ዲስ ስታንዳርድ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችን ለማናገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.