ዜና፡-በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን 14 ሰዎች መገደላቸውንና 17 ሰዎች መቁሰላቸውን እንዲሁም ከ30 በላይ ሰዎች መጥፋታቸውን የአይን እማኞች ተነገሩ

በሲያኔ መኮንን

አዲስ አበባ: ሰኔ 2/2013-በመተከል ዞን በአማኒ ቀበሌ በገበያ ላይ አንድ አዛውንት በመገደላቸው ተከትሎ ቅዳሜ በገበያ ቦታው በተከፈተ የቡድን ጥቃት በዜጎች ላይ ግድያ መፈፅሙን ለአዲስ ስታንዳርድ የደረሰው መረጃ ያሳያል፡፡

በቦታው የነበሩ በርካታ የአይን እማኝ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው አንድ አረጋዊ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በመገደሉ ምክንያት በቡለን ወረዳ ቀበሌ 02 ጠዋት በቀበሌው የሚኖሩ የተለያየ የማህበረሰቡ ክፍሎች ወደ ገበያ በሚሄዱበት ወቅት ጥቃቱ እንደተፈፀመ ተናግረዋል
በጥቃቱ አበበ ኩላሽ የሚባል የ15 አመት የአክስት ልጁ የተገደለበት ገሚር ቢቲሽ “ለገበያ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ተኩስ ተከፈተ” ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል ፡፡

ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎች እስካሁን የት እንደደረሱ አታወቀም ያለው ያለው አቶ ገሚር የኮማንድ ፖስት አባለት ወደ ቦታው ለመድረስ ከአንድ ሰአት በላይ ፈጅቶባቸዋል ሲል ከጥቃቱ የተረፉ አንዳንድ ሰዎች ሸሽተው በቀበሌ ውስጥ እና በሚያውቋቸው ሰዎች ቤት ተደብቀዋል ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል፡፡

በወረዳው የሉ ባለስልጣናት በጥቃቱ ውስጥ መሳተፋቸውን የገለፀው አቶ ገሚር መንግስት በሚከሰቱ ጥቃቶች ላ ዝምታውን መስበር አለበት ሲል “ሁሉም ኢትዩጱየዊ በማህበረሰባችን ላይ የሚደርሰውን ተደጋጋሚ ጥቃት ማውገዝ አለብን ቅሬታችን እየጨመረ ነው ፡፡ ስለኛ መሞት የሚናገርልን አካል የለም” ብሏል፡፡

የመተከል ዞን ፖሊስ ኮማንደር ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩትበጥቃቱ ላይ የተሳተፉ 28 ተጠርታሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል ምን ያህል ሰዎች ላይ ጥቃቱ እንደደረሰ የተጠየቁት ኮማንደሩ ጥቃቱ በምርመራ ላይ ነው ከማለት ውጪ መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል::

ዶ/ር ጃለታ አዳቦ የቡለን ከፍተኛ ሆስፒታል ሀኪም 14 ሰዎች የአንድ አመት ልጅን ጨምሮ በደረሰባቸው ጉዳት እንደሞቱነና ከሞቱት ውስጥ 3ቱ ሴቶች ሲሆኑ አስራ አንድ ወንዶች ናቸው በአሁኑ ሰአት 15 ሰዎች በኛ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ሁለት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ፓዊ ሆስፒታል ለከፍተኛ ክትትል ቢላኩም ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ መሄድ አልቻሉም ፡፡

ግጭቱን ተከትሎ የቡለን ወረዳ ኮማንድ ፖስት የጦር መሳሪያን ይዞ የሚንቀሳቀስ ሰው ላይ ከምሽቱ አንድ ሰአት እስከ ጠዋቱ 12 ሰአት ድረስ አግድ ጥሏል ፡፡ ከደህንነት ሰራተኖች ውጪ ማንኛውም ሰው ምንም አይነት መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም ተብሏል፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በዞኑ እና በወረዳው የአመርርነት ቦታዎች 25 የቀድሞ ታጣቂ ቡድኖችን ስልጣን ከሰጠ በውኋላ ነው፡፡ በመተከል ዞን የቀድሞ ሰላሙን ለመመለስ በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ አባላትን ስልጠና በመስጠት በተለያዩ ወረዳዎች ከማህበረሰቡ ጋር የእርቅ ስነስርአት አካሂደዋል፡፡AS

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.