ዜና፡ የደቡብ ክልል ልዩ ሀይል ከወልቂጤ ከተማ ለቆ እንዲወጣ ተወስኗል፤ የከተማዋ ነዋሪሮች ከሳምንት በኋላ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሱ ነው- የከተማዋ ነዋሪዎች
በብሩክ አለሙ @Birukalemu21 አዲስ አበባ፣ የካቲት 16/ 2015 ዓ.ም፡- የካቲት 8 በወልቂጤ ከተማ በውሃ እጥረት ምክኒያት ጄሪካን ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የፀጥታ ሃይሎች ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ ተቋርጦ የነበረውን እንቅስቃሴ በተመለከተ በሽማግሌዎች፣ በሃይማኖት አባቶች፣ በከተማ አስተዳደሩ ውይይት ተደርጎ የተከማው ማህበረሰብ ቅድመ-ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ከአንድ ሳምንት በኋላ ወደ