ዜና፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች ማስጀመሩን አስታወቀ
ፎቶ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲስ አበባ፣ መስከረም 19/2015 ዓ.ም፡- ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ ያለውን የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራው በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች ማስጀመሩ አስታወቀ። የጎንደር እና አወዳይ ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት