ዜና፡ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ እንዲሰጥ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4/2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በአማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ) ቋንቋ እንዲሰጥ እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የከተማ አስተዳደር ካቢኔው ውሳኔውን ያስተላለፈው ከብዘሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ባካሄደው በ2ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ነው፡፡

በተጨማሪም ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉም የከተማው ትምህርት ቤቶች የአገር ውስጥ ቋንቋ መማራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉንም የትምህርት አይነቶችን በእንግሊዘኛ መማር እንዲችሉ እንዲደረግ፣ ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች አረብኛና ፈረንሳይኛ በሃይስኩል ደረጃ አማራጭ ትምህርት ሆኖ እንዲቀጥልም ተወስኗል፡፡

የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት መጀመሪያ እድሜ ከ4 ዓመት እንዲሆን፣ በአዲሱ የስርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ መሰረት 11ኛ እና 12ኛ ክፍል የስራ እና ቴክኒክ ትምህርት በተለያዩ አመራጮች እንደሚማሩ፣ ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች በክላሰተር በቅንጅት እንዲሰጥና በተጠናው ጥናት መሰርት ወደ ግንባታ እንዲገባ እንዲደረግ የተወሰነ ሲሆን፣ በተጨማሪም የግል ት/ቤቶችን የመፅሐፍት እጥረት ለመቅረፍ በሽያጭ ለማቅረብ ለመጽሓፍት ህትመት የተዘዋዋሪ ፈንድ 250 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮምያ ክልል ለኦሮምኛ ቋንቋ ማስተማርያነት በውሰት ተወስዶ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ስርአተ ትምህርት በአዲሱ ስርዐት ትምህርት የሚተካ ይሆናል ተብሏል።

ነገር ግን በአንዳንድ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ግጭት እና አለመግባባት ስላስከተለው በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማን መስቀልና የኦሮሚያ ክልል መዝሙር በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡

ታህሳስ 19/ 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እና መዝሙር ጋር በተያያዘ ከተከሰተው ግጭት ለአካለ መጠን ያለልደረሱ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ማውገዙ ይታወሳል።  ኮሚሽኑ በመግለጫው እንዳስታወቀው የፖሊስ አባላት የተፈጠረውን ግጭት ለመቆጣጠር በወሰደው የእስር እርምጃ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈፅመዋል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.