ዜና፡ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ተጨማሪ የመሬት መንቀጥቀጥ ያጋጥማቸዋል ሲሉ የዘርፉ ተማራማሪ አስጠነቀቁ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2/2015 ዓ.ም፡- የካይሮ ዩኒቨርስቲ የጂኦሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት አባስ ሻራኪ ኢትዮጵያ እና ግብጽ በመሬት መንቀጥቀጥ ሊመቱ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ። በግብጽ የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በአስዋን ግድብ አቅራቢያ መሆኑን የጠቆሙት ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያ ደግሞ በህዳሴው ግድብ አቅራቢያ እንደሚሆን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ ሰሜን ምስራቅ 100 ኪሎ ሜትር