ዜና፡ የአማራ ክልል መንግስት ከዘጠኝ ወር እስር በኋላ ዘመነ ካሴን ሲፈታው፤ የፌደራል መንግስት እስክንድር ነጋን እግር በግር እየፈለገው ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28/2015 ዓ.ም፡- የአማራ ክልል መንግስት የፋኖ ታጣቂ ሀይል መሪ የነበረው ዘመነ ካሴን ትላንት ግንቦት 27 ቀን 20015 ዓ.ም ሲፈታው የፌደራል መንግስት የቀድሞው ባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር አሁን ደግሞ የአማራ አንድነት ግንባር መመስረቱ የተሰማው እስክንድር ነጋን እግር በግር እየፈለገው እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ በአማራ ክልል የባሕር ዳር