ዜና፡ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ እንዲሰጥ ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4/2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በአማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ) ቋንቋ እንዲሰጥ እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ የከተማ አስተዳደር ካቢኔው ውሳኔውን ያስተላለፈው ከብዘሃ