ዜና፡ በኢትዮጵያ እና ዩክሬን ጦርነቶች ሳቢያ በ2022 በአለማችን በጦር ሜዳ የሞቱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን አንድ ጥናት አመላከተ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ በትግራይ በ2022 ብቻ በተካሄደው ጦርነት ከ100ሺ በላይ ሰዎች በጦር ሜዳ መሞታቸውን መቀመጫውን ኖርዌ ኦስሎ ያደረገው የሰላም ጥናት ኢንስቲትዩት ይፋ ያደረገው መረጃ አመላከተ። በአለማችን በ2022 ከተካሄዱ ጦርነቶች ከፍተኛውን ሙት ያስመዘገበው በትግራይ የተካሄደው ጦርነት መሆኑን ያመላከተው ተቋሙ በሁለተኝነት የጠቀሰው በዩክሬን የተካሄደውን