ዜና፡ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃመት በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ገጭት እንዳሳሰባቸው አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11/2015 ዓ.ም፡- የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃመት በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ግጭት እጅግ እንዳሳሰባቸው በማስታወቅ በአፋጣኝ ተኩስ እንዲቆም ጠይቀዋል።

ሊቀመንበሩ በህብረቱ ድረገጽ ባስተላለፉት መልዕክት ሁኔታውን በትኩረት እየተከታተሉት እንደሚገኙ አስታውቀው የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ህገመንግስታዊ ስርአት እንዲከበር፣ ለግዛት አንድነቷ፣ ሉአላዊነቷ እና ነጻነቷን ለማስጠበቅ የሚቻለውን ነገር ለማድረግ ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

ተፋላሚ ሀይሎች ጦርነቱን እንዲያቆሙ እና ለሰላማዊ ዜጎች ከለላ እንዲሰጡም ጠይቀዋል። ልዩነቶቻቸውን ለመፍታት ሰላማዊ አማራጮችን እንዲወስዱ አሳስበዋል።

የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያውያን ተነሳሽነት ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የሚደረግን ሁሉንም ጥረቶች ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.