ዜና፡ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተከትሎ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሚመራ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ መቋቋሙ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29/2015 ዓ.ም፡- በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የጸና ይሆናል ሲሉ የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ማስታወቃቸውን የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። የፍትሕ ሚኒስትሩ በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ አተገባበር ዙሪያ ማብራሪያ መስጠታቸውን ዘገባዎቹ አመላክተዋል።

በመንግስት ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ዝርዝር እንደሚያመላክተው በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል የሚመራ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ መቋቋሙን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ የዚህን አዋጅ አላማ ለማሳካት አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን የአደባባይ ስብሰባና ሰልፍ ማድረግ፣ መደራጀት፣ በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስን የመከልከል ስልጣን እንዳለው ተጠቁሟል። በተጨማሪም የሰዓት እላፊ የማወጅ፤ ለተወሰነ ጊዜ አንድ መንገድ፣ አገልግሎት መስጫ ተቋም መጓጓዣ ዘዴ እንዲዘጋ እና እንዲቋረጥ ለማዘዝ የሚያስችል ስልጣን እንደተሰጠው አስታውቋል።

ሰዎች ለጊዜው በተወሰነ ቦታ እንዲቆዩ፣ ወደ ተወሰነ አካባቢ እንዳይገቡ ወይም ከተወሰነ ቦታ እንዲለቁ ለማዘዝ የሚያስችል ስልጣን ተሰጥቶታል ብሏል።

ተጠርጣሪዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር በማድረግ ለማቆየት የሚያስችል ስለጣን ተሰጥቶታል። ማናቸውም ከዚህ አዋጅ አላማ በተፃረረ መልኩ እየተነቀሳቀሱ እንደሆነ የተጠረጠሩ የመገናኛ ብዙሃንም ሆነ ሌሎች አካላት እንዲዘጉ፣ እንዲቋረጡ፣ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ወይም እንቅስቃሴያቸው እንዲገደብ ለማዘዝ የሚያስችል ስልጣን ተሰጥቶታል ብሏል።

የተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች እና መዋቅሮችን መልሶ ማቋቋም፣ ማደራጀት ወይም የአስተዳደር እና የፀጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ እና ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል ተብሏል።

በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለታጣቂ ቡድኖች የገንዝብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው ብሏል። ማንኛውንም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል።

አስቸኳይ ግዜ አዋጁ እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛዉም የሃሪቱ አካባቢ ተፈፃሚነት ይኖረዋል ተብሏል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.