ዜና፡ መንግስት በእስር የሚገኙትን የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር አመራሮችን በአስቸኳይ እንዲፈታ ሂዩማን ራይት ዎች ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጭ በእስር የሚገኙ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን በአፋጣኝ እንዲለቅ ሂዩማን ራይት ዎች ጠየቀ። ሰባት የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ፍርድ ቤት በነጻ ቢለቃቸውም በኦሮምያ ፖሊስ በዘፈቀደ ታስረው እንደሚገኙ የገለጸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይት ዎች አመራሮቹ ላለፉት ሶስት አመታት ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ታስረው እንደሚገኙ ጠቁሟል።

ጉዳዩ መንግስት የፍትህ ስርአቱን በአፋጣኝ ማሻሻል እንዳለበት የሚያመላክት ነው ሲልም ገልጿል። ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ሰባት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አብዲ ረጋሳ፣ ዳዊት አብደታ፣ ለሚ ቤኛ፣ ሚካኤል ቦረና፣ ኬነሳ አያና፣ ጋዳ ኦልጂራ  እና ገዳ ገቢሳ በእስር ቤት እንደሚገኙ በመግለጫው ያስታወቀው ሂዩማን ራይት ዎች ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ እንዲለቀቁ ቢያዝም አለመለቃቀቸውን አስታውቆ መንግስት ምንም አይነት የህግ መሰረት ሳይኖረው በእስር እንዳቆያቸው አመላክቷል።

የፖሊስ ባለስልጣናት የኦሮሞ የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮችን ያለምክንያት ለተራዘመ ግዜ በማሰር በኢትዮጵያ የፍትህ ስርአት ላይ እየተሳለቁ ነው ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ተቋም የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ሌተሺያ ባደር መናገራቸውን መግለጫው አካቷል። የኢትዮጵያ መንግስት ታሳሪዎቹን በአፋጣን እንዲለቅ እና በተሳሳተ መንገድ የማሰር ተግባር በመፈጸም የፖለቲካ ጭቆና ከመተግበር ከመጠቀም እንዲጠብ ሃላፊዋ መጠየቃቸውንም አስታውቋል።  

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋሙ ዘጠኝ የሚሆኑ የታሳሪዎቹን ቤተሰቦች፣ የታሳሪ ጠበቆች ቡድንን እና የኦነግ ባለስልጣናትን በስልክ ማናገሩን ጠቁሞ በተጨማሪ የፍርድ ቤት መዛግብትን እና የህክምና ማስረጃዎቹን መመልከቱንም ገልጿል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.