ዜና ፈጠራ፡ ሁለት ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተመራማሪዎች እና ቡድናቸው አዲስ የወባ መከላከያ ክትባት ማግኘታቸውን አስታወቁ

አለምታዬ አንዳርጌ እና ዮናስ አበበ

            በእጅጉ ወልዴ (ከሜሪላንድ)

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2015 ዓ.ም፡- በሮክቪል ሜሪላንድ የሚገኙ ከፍተኛ ተመራማሪዎች የወባ በሽታን ለመዋጋት ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረክታል የተባለውን የጥናት ውጤት ለአለም አቅርበዋል። ቡድኑ አለምታዬ አንዳርጌ እና ዮናስ አበበ የተባሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶችን ያካተተ ሲሆን ግኝታቸው ‘Nature’ በተሰኘው ከፍተኛ ጥራት ያለው የምርምር ውጤት በሚጣወበት የታህሳስ እትም ላይ ታትሟል

እስካሁን ድረስ 90 በመቶው የፀረ-ወባ ክትባቶች ከወባ ትንኝ ውስጥ በሚኘገው ተሕዋስያን በመጠቀም ብቻ ሲሆን እነዚህ ከፍተኛ ተመራማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ሕዋስ በቤተ ሙከራ በማምረት ውጤታማ የሆነ የፀረ-ወባ ክትባት ማግኘታቸውን ዘግበዋል።

የባርሴሎና የዓለም ጤና ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር እና የዓለም ጤና ድርጅት የወባ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ፔድሮ አሎንሶ ይህ ታላቅ የምርምር ውጤት ለክትባት ማምረቻ አስፈላጊ የሆነውን ግንዛቤያችንን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ተጽእኖ አለው ብለዋል።

የስዊስ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ማርሴል ታነር የምርምር ውጤቱን አፅንዖት ሰጥተው የቀረቡት ቴክኖሎጂዎች የፀረ-ወባ  ክትባት ማምረት ለሚፈልጉ የአለም ሀገራት በቀላሉ ሊተላለፉ የሚችሉ ናቸው ብለዋል።

ይህ ታዋቂ ጆርናል በከፍተኛ ደረጃ እና በጥራት የሚታወቅ በመሆኑ ለብዙ ተመራማሪዎች የህይወት ዘመን ምኞት ነው። ሁለቱ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት የሳናሪያ ባዮቴክ ኩባንያ ከፍተኛ ተመራማሪ ሲሆኑ አለምታዬ አንዳርጌ ባለፈው አስቸጋሪ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ከምርምር ሥራቸው በተጨማሪ ለምርምር ስራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ከተለያዩ የሽያጭ ኩባንያዎች በመለየት በጊዜው እንዲገዙ እና ሙከራዎቹ ያለምንም ችግር እንዲቀጥሉ ላደረጉት አስደናቂ አመራር እ.ኤ.አ በየካቲት2022 ምርጥ ሰራተኛ በመሆን ተሸልመዋል።

እኚህ ተመራማሪ በኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ድርጅት ተባባሪ ተመራማሪ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በአሜሪካን ሀገር ብሄራዊ ጤና ተቋም (National Institute of Health) የክትባት ምርምር ማዕከል ውስጥ አገልግለዋል። ዮናስ አበበም በኩባንያው ውስጥ የተለያዩ የፋርማሲዩቲካል ኦፕሬሽን ቡድኖችን በሃላፊነት በማሰልጠን እና ይህንንም ተግባር በተሳካ ሁኔታ በተደጋጋሚ በመወጣት፣ እ.ኤ.አ በየካቲት2019 ተሸልመዋል። 

እ.ኤ.አ በ 2020 ፣ የዓለም ጤና ድርጅት 241 ሚሊዮን የወባ በሽተኞች መኖራቸውን እና 627 ሺህ ሰዎች በተለይም ከሰሃራ በታች ያሉ ሕፃናት በወባ በሽታ መሞታቸውን ዘግቧል። በሽታው በወባ ትንኝ የሚተላለፍ ሲሆን ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ጉንፋን የመሰለ በሽታ ምልክቶቹ ናቸው። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.