አዲስ አበባ፣ህዳር 19/2015፡ በተሻሻለው የሰብአዊ እርዳታ እቅድ መሰረት ከሰኔ እስከ ሀምሌ 2015 ዓ.ም ድረስ የጸጥታ ችግር፣ ግጭቶችና ብጥብጥ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎትን መጀመሪያ ላይ ከነበረበት 3.085 ቢሊዮን ዶላር ወደ 3.335 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንዲል አድርጓታል።
ሆኖም ከ20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሕይወት አድን እርዳታ ላይ ያነጣጠረው ዋናው የ2015ቱ የሰብዓዊ እርዳታ ዕቅድ “በቂ ያልሆነ እርዳታ ነው” ሲል ሪፖርቱ አሳውቋል። “በዓመቱ አጋማሽ ላይ ከሚያስፈልገው 3.085 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሰብዓዊ እርዳታ 39.2 በመቶ ብቻ አግኝቷል። ለምግብ እርዳታ ምላሽ ያልተሟሉ 38 ከመቶ አመታዊ ፍላጎቶች አሁንም በአመቱ አጋማሽ ላይ አልተሟሉም ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሶዚ እንዳሉት በኢትዮጵያ የተቸገሩ ሰዎች ቁጥር ከዓመቱ መጀመሪያ ጋር ሲነጻጸር በ11 በመቶ ገደማ ጨምሯል። በዚህም መሠረት ቁጥሩ በ2015 ዓም መጀመሪያ ላይ ከታቀደው 20.4 ሚሊዮን ወደ 22.6 ሚሊዮን ከፍ ብሏል።
ሪፖርቱ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች 52% ህጻናት ሲሆኑ ሴቶች እና ወንዶች እያንዳንዳቸው 24% እንዲሁም አካል ጉዳተኞች 18% ናቸው ብሏል።
የግማሽ አመት ግምገማው በኢትዮጵያ መንግስት እና በሰብአዊ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ አለም አቀፍዊ እና ሃገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን “እስካሁን ድረስ ያለውን ምላሽ እና በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች አፋጣኝ የህይወት አድን እርዳታ ለሚፈልጉ ቅድሚያ እየሰጠን መሆኑን በግምገማ ተረጋገጧል” ሲል የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ተናግርዋል።
“ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች በዚህ አመት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መከራና መፈናቀልን ከፍ አድርጎታል። በደቡብ እና ሰሜን ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉ ማህበረሰቦች ከ2013 ዓ.ም መገባደጃ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ የዝናብ ወራቶች ዝናብ የሌለ መሆኑን ተከትሎ በአርባ አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ እየተሰቃዩ ነው” ሲሉ ዶ/ር ሽፈራው በሪፖርቱ ተናግረዋል።
በመላው ኢትዮጵያ የሚሰጠውን እርዳታ ለመደገፍ የሰብአዊ አጋሮች አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እየጠየቁ ነው። “የእኛ አጋሮቻችን በጣም አስቸኳይ ፍላጎቶችን ለመቅረፍ እና የህይወት አድን ፍላጎቶችን ለማስቀጠል እንደገና በማዘጋጀት ላይ ናቸው። ለሕይወት አድን ስራዎች.በዚህ አመት ከሚያስፈልገው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን 60 በመቶውን የሚወክል ተጨማሪ 1.8 ቢሊዮን ዶላር አሁንም በኢትዮጵያ ለሚደረገው ሰብአዊ ምላሽ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ያስፈልጋል> ብለዋል ዶ/ር ሶዚ። “ለጋሾች ላደረጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ አመሰግናለሁ እናም ለሰብአዊ ተግባራት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳድጉ እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመተባበር በልግስና እንዲሰጡ እጠይቃለሁ”ብለዋል።
በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ አጋማሽ በጋራ በተደረገው ግምገማ መሰርት ኢትዮጵያ በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ እልባት ባለማግኘቱ፣ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሚፈጸመው ብጥብጥ መቀጠል እና በሃገሪቱ ደቡብ እና ምስራቅ ክፍል በደረሰው የድርቅ አደጋ መስፋፋት የተነሣ ሰብዓዊ ፍላጎቶች እያደገ መጥቷል።
በትግራይ ክልል ግጭት የማቆም ስምምነት ለተሻሻለ የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት አስተዋጽኦ አበርክቷል እናም የሰብአዊ አጋሮች በክልሉ ውስጥ ለተቸገሩ ሰዎች የሚሰጡትን ምላሽ እንዲያሳድጉ አስችሏል ሲል ሪፖርቱ ገልጿል። በአፋር እና በአማራ ክልሎች የግጭቱ መጠን በመቀነሱ እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ቤታቸው በመመለሳቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እርዳታ በመደረጉ የሰብአዊ እርዳታው የጨመረ ቢሆንም “በትግራይ ድንበር አቅራቢያ ያሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ለመድረስ አስቸጋሪ ነበር”።
በተቃራኒው በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሰብአዊ እርዳታ ተግባራት በፀጥታ እጦት እና ተደራሽነት ምክኒያት በከፍተኛ ሁኔታ ተገድበዋል፣ “በዚህም ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች የሰብአዊ አጋሮች ቀንሰዋል ወይም አልነበረም። አንዳንድ በኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች (ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ እና ጉጂ ዞኖች) እና ቤንሻንጉል ክልሎች ተደራሽ ባለመሆናቸው የምግብ ዕርዳታውን በዘላቂነት ለማድረስ እንቅፋት ሆነዋል።
ከጤና፣ ምግብ፣ ከትምህርት፣ ከሎጂስቲክስ እና የግብርና ምርታማነት በተጨማሪ ግጭቶች፣ ድርቅና ጎርፍ ተደምረው የሃገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ድጋፍ ከሚሹ ናችው። በመላ አገሪቱ ወደ 17.5 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች የግብርና ግብዓት ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። “የግብርና ግብአቶች በተለይም የማዳበሪያ እና ዋና የሰብል ዘር አቅርቦት ውስንነት በዋናው የግብርና ወቅት ትልቅ ስጋት ነው” ሲል ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ የብር የዋጋ መቀነሱና ከፍተኛ የዋጋ ንረት በመከሰቱ ደካማ የኢኮኖሚ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፣ “ይህም በገበያ ላይ ጫና እየፈጠረ፣ የሸቀጦችና የምግብ ዋጋ ንረት እያስከተለ ነው። አንዳንድ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችና የምግብ ሸቀጦች አቅርቦት ላይ ተፅዕኖ ያሳደረው የሩስያ እና የዩክሬን ግጭት ሁኔታውን አባብሶታል”።አስ