ዜና: የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት(ሲአርኤስ) በአማራ ክልል ቆቦ ከተማ ሁለት ሰራተኞቹ በጥይት መገደላቸውን አስታወቀ


አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3/2015 ዓ.ም፡- ፌደራል መንግሥት ሲያከራክር የቆየውን የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም በአማራ ክልል እየተደረገ ያለው ተቃውሞ እየተባባሰ በመጣበት ወቅት የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት(ሲአርኤስ) ሁለት ሠራተኞች ባለፈው እሁድ በድርጅቱ ተሸከርካሪ ውስጥ በአማራ ክልል ውስጥ በጥይት መገደላቸውን ድርጅቱ አስታወቀ፡፡ ድርግቱ በግድያው ማዘኑንም ገልጧል፡፡

ሲአርኤስ ትላንት ባወጣው መግለጫ የደኅንነት ኃላፊ ቹል ቶንግይክ እና ሹፌሩ አማረ ክንደያ እሁድ ዕለት ከተመደቡበት ሥራ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ እያሉ መገደላቸውን አስታውቋል፡፡ የግድያው ዝርዝር መረጃ አልታወቀም ያለው ድርጅቱ ነገር ግን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ኪም ፖዝኒያክ ግድያው የተፈፀመው በቆቦ ከተማ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ እሁድ እለት የከባድ መሳሪያዎች ድምጽ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎቹ ለአዲስ ስታነዳርድ አስታውቀዋል።

“ድንጋጤያችን እና ሀዘናችን ወደር የለውም፤ በዚህ ትርጉም አልባ ሁከት አዝነናል፣ ሲአርኤስ በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ለማገልገል የሚሰራው የሰብአዊ እርዳታ ድርጅት ነው “ ያሉት የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዘመዴ ዘውዴ አክለውም “ ድርጅቱ የኢትዮጵያን ህዝብ መደገፍ እንደሚቀጥል ያላቸውን ቁርጠኝነት” ገልጸዋል።

ፌደራል መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች ሰልፎች እየተካሄዱ ሲሆን በአንዳንድ ከተሞች በመንግስት የጸጥታ ሀየሎች መካከል ግጭት መፈጠሩን ነዋሪዎች አስታውቀዋል።

ይህንንም ተከትሎ በርካታ ከተማዎች ላይ የተለያዩ ክልከላዎች እየተደረጉ ይገኛል፡፡ፌደራል መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞጭ ተቃውሞ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት የክልል ልዩ ሀይሎችን እንደገና የማደራጀቱ እንቅስቃሴ ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ የመንግስታቸውን ቁርጠኛ አቋም አስታውቀዋል።
.
የጠቅላይ ሚንስቴሩን ውሳኜ በመቃወም አብን በተከታታይ መግለጫ እያወጣ ሲን ዛሬ ይፋ በደረገው መግለጫውም በአማራ ክልል ለከፍተኛ አለመረጋጋት እና የጸጥታ ችግር እየቀጠለ በመሆኑ ገዥው ፓርቲ ውሳኔ እስኪቀለበስ ጠይቋል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.