ዜና ትንታኔ: በአማራ ክልል ሞጣ ከተማ በፋኖ እና በክልሉ የጸጥታ ሀይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

በጌታሁን ጸጋዬ 

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 2014 – በአማራ ክልል ሞጣ ከተማ በጸጥታ ሃይሎች ላይ ግድያ በመፈጸሙ የአካባቢው ፋኖ አባላት እጃቸው አለበት ተብሏል። በከተማው በአማራ ክልል የጸጥታ ሃይሎች ከፋኖ ጋር በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት መጥፋት እና የአካል ጉዳት ደርሷል ሲል ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል። የሞጣ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ትናንት እሁድ ማንነታቸው ያልታወቁ “በፋኖ ስም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ” ያላቸው ቡድኖች አራት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎችን ገድለዋል ብሏል።

 በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ሰዎች መቁሰላቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል። ዋዜማ ራዲዮ እንደዘገበው የፋኖ መሪ በመንግስት ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት ነግሷል። በፋኖ አባላት እና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት የፋኖ አባላት እየወሰዱት ያለው ወታደራዊ ስልጠና እንዲቆም የመንግስት ሃይሎች ያቀረቡትን ጥያቄ ነውም ተብሏል። በዘገባው ስሙ ያልተጠቀሰው የፋኖ መሪ ፍቃደኛ ባለመሆኑ  ለእስር እንደተደረገ ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል። ዘገባዉ በዚህ የተነሳ  ግጭት መቀስቀሱን ጠቅሶ የከተማዋ ነዋሪዎችን እንደገለጹት በተኩስ ልውውጡ በትንሹ 6 ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። ተጨማሪ የጸጥታ ሃይሎች መሰማራታቸውን ተከትሎ በከተማዋ መረጋጋት መፈጠሩን ዘገባው ዘርዝሯል።

ዋዜማ ራዲዮ በጊንደ ወይን፣ በየጁቤ እና በቢውኝ ወረዳዎች በክልሉ መንግስት ታጣቂዎች እና የፋኖ አባላት መካከል ግጭት መፈጠሩን አስታውሷል። “በፋኖ እና በክልሉ መንግስት ሃይሎች መካከል ያለው ውጥረት በጣም አሳሳቢ ነው” ያለው ዘገባው “መንግስት የፋኖ መዋቅርን ለማፍረስ እያሰበ ነው በሚል ስጋት የፋኖ አባላትን ወታደራዊ ስልጠና በድብቅ መካሄድ ተጀምሯል” ብሏል።

የሞጣ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ዛሬ ማለዳ ላይ ባወጠው መግለጫ እሁድ እለት ማንነታቸው ያልታወቁ የጸጥታ ሃይሎች በፈጸሙት ጥቃት አራት የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ገልጿል። የከተማ አስተዳደሩ አክሎም በፋኖ ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ከሌሎች ወረዳዎች ጭምር በመሰባሰብ በከተማዋ ላይ ጥቃት ፈጽሟል ብሏል። የታጠቁ ሃይሎቹ  በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አየን ብርሃን ቀበሌ  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ተሽከርካሪን በመቀማት እንዲሁም ከፖሊስ ሃይሎች መሳሪያዎችን በኃይል መዉሰዳቸዉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቋል።

 መግለጫው ከተማዋን በመጠበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት የተገደሉትን አራት የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ስም ዝርዝር ዘርዝሯል። ተጨማሪ የፖሊስ አባላት እና ሚሊሻዎች ቆስለዋል ያለው መግለጫው በፀጥታ ሀይሎቹ ግድያ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። የከተማዋ ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ከተማዋን ለማተራመስ እየተሰራ ያለውን ሴራ ለመከላከል  እርምጃ እንዲወስዱ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

 የፋኖ ድርጅታዊ መዋቅር ላለፉት ወራት በስፋት አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል።  በፌዴራልም ሆነ በአማራ በክልል የጸጥታ  መደበኛ መዋቅሩ አካል ያልሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ወንዶችና ሴቶች የታጠቁ ፋኖዎች ግን ከፌደራልና ከክልል ሃይሎች ጎን ሆነው ከትግራይ ሃይሎች ጋር እየተካሄደ ያለው  ግጭት ላይ ሲሳተፉ እንደነበር አይዘነጋም።

የአማራ ክልል ርዕሰ መዲና የሆነችው ባህርዳር የፀጥታው ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት በህዳር ወር የፋኖ አባላት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መዋቅር እንዲመዘገቡና እንዲደራጁ ጥሪ አቅርቦ እንደ ነበረ ይታወሳል። የጸጥታው ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት በፋኖ መዋቅር ሰልጥኖና ተደራጅቶ ነገር ግን በመንግስት የጸጥታ መዋቅር ስር መግባት ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው የከተማ አስተዳደሩ የሎጂስቲክስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብቶ ነበር። ከክልሉ ሰላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት እውቅና ውጪ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የጦር መሳሪያ ይዘው የተገኙ አካላት በጸጥታ ሃይሎች እንደሚጠየቁም በዛኑ ወር ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

በተመሳሳይ ፣ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ በፌዴራል መንግስት ተዘጋጅቷል የተባለው እና በሰፊው ተሰራጭቶ የነበረ ሰነድ የአማራ ክልልን ጨምሮ የተለያዩ ክልላዊ መንግስታት ያጋጠሟቸውን የጸጥታ ችግሮች በዝርዝር ገልጾ በሰላማዊ ዜጎች እና ህገወጥ ታጣቂዎች በተለይም በፋኖዎች መካከል ያለውን የጦር መሳሪያ ወደ ግል የማዞር ተግዳሮቶች ላይ ተወያይቷል። በዛው ወር የጸጥታው ምክር ቤት ከትግራይ ሃይሎች እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት ያላቸው ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና ኢ-መደበኛ ሃይሎች መኖራቸውን ተወያይቶ እንደነበረ ይታወሳል። የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የቀድሞ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ መደበኛ ባልሆኑ ሀይሎች ላይ የተደረጉ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ ገጸዋል። ይህንን ተከትሎ የአማራ ክልል ባለስልጣናት እና አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቡን በመቃወም ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።

 የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በወቅቱ እንደተናገሩት መንግስት ለአገርና ለሕዝብ ነፃነት መስዋዕትነት የከፈሉትን የፋኖ አባላትን “ያደራጃል” እንጂ “ትጥቅ አይፈታም” ብለዋል። አቶ ግዛቸው በአማራ ህዝብ ታሪክ ፋኖዎች አማራውን “ከጠላት እና ውርደት” በመጠበቅ የአማራን ህዝብ በልማትና በፖለቲካዊ አካባቢዎች ተጠቃሚ ለማድረግ መስዋዕትነት ከፍለዋል። ስለዚህ መንግስት ፋኖዎችን የበለጠ ያደራጃል እንጂ ትጥቅ አይፈታም” ብለዋል።  መንግሥት ትጥቅ የሚፈታበት ምንም ምክንያት እንደሌለው የተናገሩት አቶ ግዛቸው፣ መንግሥት ዓላማው ፋኖዎችን ትጥቅ ማስፈታት ሳይሆን፣ ለአገራቸው ሲሉ የተጎዱትን ለመርዳት እንደሆነ አስረድተዋል።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በጥር ወር መጨረሻ   ባወጠው መግለጫ ፋኖ መደበኛ ያልሆነ ሃይል ሳይሆን “በሰላም ጊዜ ሙያዊ ተግባራትን እየፈፀመ አገር ከሚደርስበት ወረራ እና መፈናቀል የመከላከል ህዝባዊ ሀይል ነው” ብሏል። ባልደራስ አክሎም በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ባለስልጣናት መካከል እየተካሄደ ነው ስለተባለው ድርድር ባለሰባት ነጥብ ምክረ ሀሳቦችን አቅርቦ ነበር።

 “ፋኖ፣ በጊዜያዊነት ተሰባስቦ በአገር ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ሙሉ በሙሉ እስከሚወገድ በዱር በገደሉ እየተሰማራ፣ አካባቢውንና አገሩን ከጥቃት የሚከላከል ህዝባዊ ኃይል እንጂ፣ቋሚ የሆነ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት አይደለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን ብንጠቅስ እንኳን፣ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ወርሮ በነበረበት ጊዜ ይህ እውነታ በውል ታይቷል፡፡ ›› ሲል ፓርቲው ተናግሯል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.