ዜና: የአሶሽየትድ ፕረስ ጋዜጠኞች ላይ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን እንዲያቀርብ ትእዛዝ ተሰጠ

አሶሽየትድ ፕረስ ጋዜጠኛ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ

በማህሌት ፋሲል @MahletFasil

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25 2014 – የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የግዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ የቀረቡት የአሶሽየትድ ፕረስ ጋዜጠኞች ላይ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን የዞ የፊታችን ሰኞ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ:: ጋዜጠኛ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ ላይ ፖሊስ ምርመራን ስላልጨረስኩ 14 ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ ሲል በድጋሚ ጠይቋል።

ሆኖም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ በማዘዝ ቀጣዩን ችሎት ለሰኞ የካቲት 28/2014 ቀን ቀጥሯል::

ዛሬ በዋለው ችሎት መርማሪ ፖሊስ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ በእስር በነበሩበት ወቅት የተለያዩ ስራዎችን ሰርቼያለው ሲል ለችሎት ያስረዳ ሲሆን የተከሳሽ ቃል መቀበሉን ፣ከተጠርታሪዎች እጅ የተያዙ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ለብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ምርመራ እንዲደርግ መላኩን ፣እንዲሁም መስሪያ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹን በተመለከተ የቴክኒክ ማስረጃ እንዲልክ መጠየቁን ያስረዳ ሲሆን በቀጣይ የላኩዋቸውን መረጃዎች መሰብሰብ ስለሚቀረኝ 14 ቀን ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። ፍርድ ቤቱ የዘጠኝ ቀናት ጊዜ በፈቀደለት ባለፈው ችሎት ፖሊስ ተመሳሳይ ክርክር ተጠቅሟል

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ የጠየቀው ቀን መሰጠት የለበትም ያሉ ሲሆን “ፖሊስ በመጀመሪያ ግዜ ቀጠሮ የጠየቀውን ነው አሁን በድጋሚ እየጠየቀ ያለው :: ይህ የሚያሳው ፖሊስ ስራውን በትክክል እየሰራ እንዳልሆነ ነው ስለዚ ፖሊስ የጠየቀው ምርመራ ቀን ሊሰጠው አይገባም” ሲሉ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል::

በታህሣሥ ወር አጋማሽ ላይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን (ኦነግ ሸኔ) በአለም አቀፍ ደረጃ ያስተዋውቃሉ ያላቸውን ሁለት ጋዜጠኞች እና አንድ ካሜራማን ማሰሩን አስታውቋል። መግለጫው “በምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ ሸኔን ለማስተዋወቅ ብዙ ገንዘብ የተከፈላቸው ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው እየተመረመሩ ነው” ብሏል ። በእስር ላይ በነበረበት ወቅት ከገዥው ፓርቲ ፋናቢሲ ጋር ሲሰራ የነበረው አዲሱ ሙሉነህ ከእስር ተፈቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.