ዜና: በአማራ ክልል የሰዓት እላፊ ገደብ ሙሉ ኃላፊነት ለከተማ አስተዳደሮች ተሰጠ

አዲስ አበባ ታህሳስ 28/ 2014 – የአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት የሰዓት እላፊ ገደብ ሙሉ ኃላፊነት ለከተማ አስተዳደሮች በመስጠት የፀጥታ ሁኔታውን እየገመገሙ በራሳቸው ሰዓት እላፊ ገደቡን የማንሳትም ኾነ የማስቀጠል ሙሉ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር መስጠቱን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ገለጹ።

ከአሁን ቀደም ምክር ቤቱ የሰዓት እላፊ ገደብ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 መንቀሳቀስ እንደማይቻል ውሳኔ ማሳለፉ እና ይህም በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወሳል፡፡ አቶ ግዛቸው እንደገለጹት አስተዳደር ምክር ቤቱ ያለውን ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የሰዓት እላፊ ገደቡን በተመለከተ በትናንትናው እለት ውይይት አድርጎ ነበር።

በዚህም መሠረት ከአሁን ቀደም ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ሙሉ ኃላፊነት ለከተማ አስተዳደሮች በመስጠት የፀጥታ ሁኔታውን እየገመገሙ በራሳቸው ሰዓት እላፊ ገደቡን የማንሳትም ኾነ የማስቀጠል ሙሉ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር የተሰጣቸው መሆኑን ምክር ቤቱ  ውሳኔ አሳልፏል፡፡ አ.ስ.

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.