ትንተና:-ለብዙዎች ተስፋ የሆነው የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ

በእቴነሽ አበራ

አዲስ አበባ ታህሳስ 27/ 2014 – ከተቋቋመ  32 የሞላው የኢትዮጵያ ህፃናት መርጃ ብቸኛው በህፃናት የልብ ህመም ላይ የሚሰራ ብቸኛው ግብረሰናይ  ተቋም ነው። በተቋሙ ስር የሚገኘው የኢትዩጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል በመላው ሀገሪቱ ላሉ የልብ ታካሚዎች ህፃናት ህክምናን ይሰጣል።

እሱባለዉ የ12 አመት ሲሆን የመጣው ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ውሰጥ ከምትገኘው ሆሳእና ከተማ ነው።  የእሱባለው አክስት አስቻለች በላይ ለአዲስ እስታንዳርድ እንደገለፀችው የእሱ ባለውን የልብ ህመም ያወቁት በጨቅላነቱ ነው ። “ላለፉት አስር አመታት ክትትል ነበረው ከረጅም ጥበቃ በኋላ ተራችን ደርሶ ባለፈው ሳምንት የቀዶጥገና ህክምና ተደርጎለታል።” አስቻለች ለተደረገላቸው የነፃ ህክምና እንዲሁም ማእከሉ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገኙ የልብ ታማሚ ህፃናትን በመርዳቱ እና የቤተሰቦቻቸውን የገንዘብ ችግሮች በማቅለሉ  በጣም ታመሰግናለች። 

ሌላው የማእከሉ ተጠቃሚ የሶስት ልጆች አባት የሆኑት የደብረ ማርቆሱ አባይነህ ደበበ ናቸው። አባይነህን ያወራናቸው ለወንድ ልጃቸው ቀዶጥገና አዲስ አበባ መጥተው ነው። “የስድስት አመት ሴት ልጄ እና የስምንት አመት ወንድ ልጄ ነበሩ በልብ ህመም የሚሰቃዩት ፈጣሪ ይመስገን ሴቷ ልጄ ከሳምንታት በፊት ተራዋ ደርሶ ቀዶ ጥገናው ተስርቶላታል አሁን የቀረው የወንዱ ነው እርሱም በቅርቡ ይሰራለታል።”

የህፃናት የልብ ህሙማን ማእከሉ ካሉበት ተግዳሮቶች የተነሳ በሙሉ አቅሙ እየሰራ እንዳልሆነ የተቋሙ የህዘብ ግንኙነት ሀላፊ ናሆም ስንታየሁ ለአዲስ እስታንዳርድ ገልጸዋል ። 

የማእከሉ ተግዳሮቶች 

እንደ ናሆም ገለፃ ማእከሉ በቀን ከ10 -12 የሚደርሱ  የልብ ታማሚ ህፃናትን በ ሪፈራል ይቀበላል። “ማእከላችን በሙሉ አቅሙ ቢሰራ በ አመት እስከ 1500 ቀዶጥገናዋች ማድረግ ይችላል ነገርግን በአቅም ውስንነት ምክንያት እያከናወንን የምንገኘው 500 ቀዶጥገናዋችን ብቻ  ነው ።” ሀላፊው አክሎም “በጀመርነው የጎርጎሮሳዊያኑ አመት እቅዳችን የቀዶ ህክምና አቅማችንን ወደ 720 ማሳደግ ነው።”

አሁን ላይ የታካሚዎችን የህክምና ሰነዶች ከወረቀት ወደ ዲጂታል እየተቀየረ ስለሆነ ትክክለኛ ለቀዶ ጥገና የሚጠብቀው ታካሚ ብዛት ማወቅ አይቻልም እንደ ናሆም ማብራሪያ ነገር ግን አዲስ እስታንዳርድ ከሁለት አመት በፊት በተመሳሳይ ወቅት የሰራው ዘገባ 7000 የልብ ታካሚ ህፃናት ለቀዶ ህክምና እየተጠባበቁ እንደነበር ያሳያል። እንደ ናሆም ገለፃ 16%  የሚሆነው የኢትዮጵያን ህዝብ የልብ እና ተዛማች ችግሮች ያጋጥሙታል፡፡ ከከዚህ ቀደሙ በተለየ ያለፉት ሁለት አመታት በአለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የጤና፣ የኢኮኖሚ እና የማህበረሰብ ቀውስ የፈጠረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ የማእከሉንም እንቅስቃሴ ጐድቶታል።

” በሀገራችን ወረርሽኙ የተከሰተ ወቅት የትራንስፖርት ማጣት ታካሚዋቻችንን አጋጥሞ ነበር እንደ ግዜዊ ችግር ነገር ግን  በፍጥነት የስልክ መስመር አዘጋጅተን ክትትላቸውን እንዲቀጥሉ አድርገናል።  በተጨማሪም ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ያወጣውን የ ኮሮና ቫይረስ የጥንቃቄ መመሪያን ስለምንከተል የህፃናቱን አስታማሚዋች እዚሁ ማእከል ውስጥ ስለሚቆዪ ተጨማሪ ወጭ ሆኖብናል።”

እንደ ናሆም ማብራሪያ ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች በላይ የሚብሰው የህክምና ግብአቶች እጥረት ነበር ምክንያቱም ከ 80 % በላይ የሚሆነው ግብአት ከውጭ ሀገር ነው የሚመጣው።” የህክምና ግብአቶች እጥረት ከ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ፣መሰል ተቋማት ፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያን ማህበረሰብ ጤና ተቋም እርዳታዋች ለመቅረፍ ብንችልም ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እርዳታ መቀዛቀዝ አጋጥሞን ነበረ ። እንደማሳያ ኢትዪ ቴሌኮም በነፃ ያቀረበልን 6710 ማእከሉን በገንዘብ መደጎሚያ መስመር በወር ሲያስገባ ከነበረው 300,000 – 400,000 ወደ 30,000- 40,000 ወርዶ ነበር ወርሺኙ ባስከተለው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ምክንያት”።ከላይ የተዘረዘሩት ተግዳሮቶች ቢኖሩም አዲሱ የጐሮጐሮሳውያኑ አመት ለማእከሉ  ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ተስፋ አድርጓል።

” በጎ ፍቃደኛ ግለሰቦች እና ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ የሚገኙ ተቋማት በተለያየ መንገድ እየረዱን ነው፡፡ ይሄ እርዳታ ከተማሪዋች ጀምሮ ሁሉንም አይነት ባለሙያዎቸ ያካትታል ለምሳሌ የናዝሬት  ትምህርት ቤት ተማሪዎች በራሳቸው ፕሮግራም አውጥተው የህክምና ሰነዶችን ከወረቀት ላይ በሌላ የህክምና ማስረጃዋች ማደራጃ ሶፍትዌር ማቅረቢያ ድርጅት በተበረከትልን ሲስተም  መረጃዎችን በማስገባት ሲያግዙን ነበር።። በተለይም ባንኮች እና ሌሎች የገንዘብ ተቋማት ሀላፊነታቸው እየተወጡ ስለሆነ ምስጋና ይገባቸዋል ሌሎችም ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።”

የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ከ አዲስ አበባ ውጭ የሚመጡ ታካሚዋች ማእከሉ ላይ የሚያሳድሩትን ጫና ለመቀነስ ከክልል ዪንቨርሲቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ነግረውናል። “ከ ሀዋሳ እና ጎንደር ዪንቨርስቲዋች ጋር አብረን ለመስራት የ መግባቢያ ሰነድ የተፈራረምን ሲሆን ከጂግጂጋ እና አርሲ ዩንቨርሲቲዋች ጋርም አብረን ለመስራት ንግግር ላይ እንገኛለን። ከዪንቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታሎች ጋር አብሮ መስራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት። መንግሰት ስለሆነ የሚያቀርብላቸው የግብአት ችግር ብዙ አያጋጥማቸውም ቢያጥራቸው እንኳን በቀላሉ በመንግስት የግዢ አቅርቦት ከውጭ ማስገባት ይችላሉ ፤ ታካሚዋች በአቅራቢያቸው ሳይጉላሉ ህክምና ያገኛሉ ለእኛ ደግሞ ጫና ስለሚቀንስልን በፍጥነት ለመስራት ያስችለናል፡፡”

ናሆም ሲያብራራ ይህ የህፃናት የልብ ማእከል ሲቋቋም ሶስት አላማዎችን ይዞ ነወ። የልብ ማእከሉን መገንባት፣ በሰው ሀይል እና የህክምና ግብአቶች ማሟላት እና ቋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ በመፍጠር የተቋሙን ቀጣይነት መረጋገጥ ናቸው ። ሀላፊው ሲያሰረዱ ማእከሉ አሁን ላይ በሶስተኛው አላማው ማለትም ቋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ በመፍጠር ዘላቂነቱን ማረጋገጥ ላይ እየሰራ ነው። ለዚህም የሚያግዝ እቅድ አውጥተን እየሰሩ እንደሆነ ለአዲስ እስታንዳርድ አስረድተዋል ።

” የማእከሉ  25 % የሚሆነው ወጭ የሚሸፈነው የአዲስ አበባ አስተዳደር ከሊዝ ነፃ በሰጠን ቦታ ላይ ሲሆን ባሉን ሁለት ህንፃዋች ሲሆን ሶስተኛውን ህንፃ ለመጨረስ አሁንም ድጋፍ እንፈልጋለን ።” የማእከሉ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ  በመጨረሻ መልእክታቸው ለማእከሉ የሚደረገው እገዛ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ” ከችግሩ ጥልቀት የተነሳ በሙሉ አቅማችን ብንሰራ እንኳን ሙሉ በሙሉ ችግሩን መቅረፍ አንችልም ሁለት ወይም ሶሰት መሰል ተቋማት ያስፈልጉናል እስከዚያው ድረስ ግን ይህንን ተቋም ማጠንከሩ ላይ እነድንሰራ እጠይቃለሁ። ሀገር ውስጥ ከሚደረገው በተለያየ መንገድ ከሚደረገወ ድጋፍ በተጨማሪ በተለያዩ ባንኮች ውስጥ በውጭ ሀገር ለምትኖሩ በጎ አድራጊዋች  ታስቦ የተዘጋጀ አካውንት ስላለ የምትችሉትን እንድትለግሱ አደራ እላለሁኝ።”

የበጎፈቃድ አምባሰደር በተግባር

የህፃናት የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል  ከሶስት አመት በፊት ተዋናይት መሰረት መብራቴን የበጎፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሰይሟል። መሰረት ከምትታወቅበት የትወና እና የማስታወቂያ ባለሙያነት ውጭ በተለያዩ የበጎፍቃደኝነት ስራዋቿ ትታወቃለች። የማእከሉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ እንደሚገልፁት መሰረት እያደረገችው ባለው እንቅስቃሴ እና ማስተዋወቅ ማእከሉ ተጠቃሚ ሆኗል።”ለምሳሌ ባለፈው መስከረም ወር ወደ አሜሪካ ተጉዛ የኢትዩጵያውን ቀን ሲከበር ከ ስድስት ሚልየን በላይ በካሽ እንዲሁም የተለያዩ የህክምና ግብአቶችን አሰባስባ ለወደፊትም በቀላሉ በጎ አድራጊዋች መለገስ የሚችሉበትን መንገድ አመቻቸታ ነው የመጣችው ለዚህም በህፃናቱ ስም ከልብ እናመሰግናታለን።” አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.