ዜና: ሳዑዲ አረብያ ዜጎቿ ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞችን እንዲቀጥሩ ከሶስት አመታት በኋላ ፈቀደች፤ ኤጀንሲዎች የሚጠየቁት የቅጥር ክፍያ ጣሪያ እጅግ አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል

ፎቶ ከsaudi-expatriates ድረገጽ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5/ 2015 – የሳዑዲ አረብያ መንግስት ዜጎቹ ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞችን እንዲቀጥሩ ከሶስት አመታት በኋላ መፍቀዱን ይፋ አደረገ። በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የቤት ሰራተኛ የሚመለምሉ ኤጀንሲዎች ኢትዮጵያውያንን ሲቀጥሩ ቅጥሩን ለመፈጸም ከሳዑዲ መንግስት የሚጠየቁት የቅጥር ክፍያ ጣሪያም ተቀምጧል። በተቀመጠው የክፍያ ጣሪያ መሰረትም አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ በሳዑዲ አረብያ ለማሰራት መልማይ ኤጀንቶች እና ተቋማት ለሳዑዲ መንግስት የሚፈጽሙት ከፍተኛ የቅጥር ክፍያ 6900 የሀገሪቱ ገንዘብ ሪያል ወይንም 1840 የአሜሪካ ዶላር የማይበልጥ መሆኑም ተገልጿል። ክፍያው ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይንም ቫት ሳይጨምር መሆኑም ተመላክቷል።

የሳዑዲ አረብያ የሰው ሃብት እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር እንዳስታወቀው በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የቤት ሰራተኛ መልማይ ኤጀንሲዎች እና ተቋማት ከተቀመጠው የክፍያ ጣሪያ በላይ ክፍያ እንደማይፈጽሙ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከሌሎች ሀገራትም የሚመለመሉ የቤት ሰራተኞችን በተመለከተ ኤጀንሲዎች የሚጠበቅባቸው የክፍያ ጣሪያ ይፋ ማድረጉን ዛውያ የተሰኘ ድረገጽ አውስተዋል። ለሌሎች ሀገራት መልማይ ኤጀንሲዎች የተቀመጠው የቅጥር ክፍያ ጣሪ ለኢትዮጵያውያን ከተቀመጠው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ከፍተኛ መሆኑም ተጠቁሟል። ከፍተኛው ከፍያ 17ሺ 288 ሪያል ለፍሊፒኖ የቤት ሰራተኞች ሆኖ ተቀምጧል። የኢትዮጵያ ጎረቤት ከሆነችው ኬንያ ለሚመለመሉ የቤት ሰራተኞች ኤጀንሲዎች የሚጠበቅባቸው የቅጥር ክፍያ ጣሪያ 10ሺ 870 ሲሆን ለብሩንዲ የቤት ሰራተኞች 7ሺ 500 ሪያል፣ ለኡጋንዳ ደግሞ 9ሺ 500 ሪያል ሆኖ ተቀምጧል።

በሳዑዲ አረብያ በርካታ ኢትዮጵያውያን በህጋዊ እና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በመግባት እንደሚኖሩ ይታወቃል። ከሁለት አመት በፊት አዲስ ስታንዳርድ ባስነበበው የምርመራ ዘገባ በህገወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረብያ የገቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤቶች ታጉረው ከፍተኛ ስቃይ እያሳለፉ እንደሚገኙ ተመላክቷል። በወቅቱ በህገወጥ መንገድ ብቻ ሳይሆን በህጋዊ መንገድ የገቡ ኢትዮጵያውያንም በማጎሪያ እስርቤቱ እንደሚገኙ እማኞችን ዋቢ በማድረግ ተገልጿል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.