ዜና፦ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የከተማ ትራንስፖርት ዋጋ ከነገ ጀምሮ መጨመሩን አስታወቀ

የአዲስ አበባ፦ ጥር 12/ 2015 ዓ.ም. – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ጭማሬ መነሻ በማድረግ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ዋጋ ከነገ ጀምሮ መጨመሩን አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት ለሚኒባስ የታክስ ተሸከርካሪዎች የጉዞ ርቀት በኪሎ ሜትር እስከ 2 ነጥብ 5 ርቀት በነባር የክፍያ ታሪፍ 3 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በተስተካከለው ታሪፍ ጭማሬ 4 ብር፣ ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 6 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ደግሞ 7 ብር ሆኗል፡፡

በተጨማሪም ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 10 ብር የነበረው ታሪፍ በተመሳሳይ 10 ብር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

የሃይገርና የቅጥቅጥ ታክሲዎች የዋጋ ጭማሪን በሚመለከት እስከ 8 ኪሎ ሜትር 5 ብር የነበረው ታሪፍ በነበረው እንዲቀጥል፣ ከ8 ነጥብ 1 እስከ 12 ኪሎ ሜትር 7 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ክፍያ በአዲሱ ታሪፍ ጭማሬ 8 ብር፣ ከ12 ነጥብ 1 እስከ 16 ኪሎ ሜትር 9 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው ታሪፍ ከነገ ጀምሮ 10 ብር እንዲሆን ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም ከ16 ነጥብ 1 እስከ 20 ኪሎ ሜትር 12 ብር የነበረው ክፍያ በአዲሱ ታሪፍ ጭማሬ 13 ብር፣ እንዲሁም ከ20 ነጥብ 1 እስከ 24 ኪሎ ሜትር 14 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው 15 ብር፣ ከ24 ነጥብ 1 እስከ 28 ኪሎ ሜትር 17 ብር የነበረው ደግሞ 18 ብር እንዲሆን የ ከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ውሳኔዉን አሳልፏል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.