ዜና፡ ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ለአንድ ቀን ስራ ጉብኝት  ሱዳን ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 18/2015 ዓ.ም፡- ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ እና ልዑክ ቡድናቸው ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ካርቱም መድረሳቸውን የጠቅላይ ሚንስቴት ጵ/ቤት አስታወቀ፡፡ ልዕክ ብድኑ ሱዳን ካርቱም ሲደርሱም የሱዳን ሪፐብሊክ የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፈታሕ አል ቡርሃን አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ባለፈው አመት ኬንያ በተካሔደው የኢጋድ ስብሰባ ላይ በአካል ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን መሪዎቹ ብሄራዊ የፖለቲካ እና የፀጥታ ችግሮችን በዲፒሎማሲያዊ መንገድ በጋራ ለመፍታት መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጠዋል፡፡

ባለፈው አመት ህዳር ወር ላይ ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ከሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት የሱዳን ወታደራዊ መሪ አባል ኢብራሂም ጋቢር ጋር ተገኛኝተው በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው ሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚንስቴሩ እና የኢብራሂም ውይይት የተደረገው የሱዳን እና የኢትዮጵያ የስለላ ድርጅቶች ሁለቱ አገራት የሽብር ወንጀልን ለመካከል መረጃ ለመለዋወጥ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከገለፁ ከአንድ ቀን ከኋላ ነው፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ካርቱም በሄዱበት ወቅት ሲሆን ስምምነቱን ከሱዳኑ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎች ዳይሬክተር አህመድ ኢብራሂም ጋር ነው የተፈራረሙት፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ያሉ ውጥረት የተባባሰው ሰኔ 27 ሱዳን ሰባት የኢትዮጵያ ሰራዊት ሰባት የሱዳን ወታደሮችንና አንድ ሲቭልን ይዘው ገድለዋል ብላ ከከሰሰች በኋላ ነው፡፡ ኢትዮጵያ “ሰዎቹ ሞቱት በሱዳኑ ሰራዊት እና በአከባቢው ሚሊሻ መካከል በተነሳ ግጭት በሞኑን በመግለፅ በቅርቡ ምርመራ ይደረጋል” ስትል ገልፃለች፡፡

ከዚያን ጊዜ በኋላ ሁለቱ ሀገራት ውጥረቱን አርገበዋል። በባለፈው አመት ሐምሌ ወር የሱዳን ወታደራዊ ሀይል ቃልአቀባይ ብርጋዴል ጀነራል ናቢል አብደላህ አሊ የሱዳን የጸጥታና ደህንነት ካውንስል የቴክኒክ ኮሚቴ ሃላፊ የጋላባት የድንበር መተላለፊያ በድጋሜ እንዲከፈት ማዘዛቸውን አስታውቀዋል። የጋለባት ኬላ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነት ቁልፍ መተላለፊያ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ከሐምሌ 17 ጀምሮ ከፍት ተደርጓል።

ነገር ግን የሱዳን የጸጥታ ሀይሎች በአወዛጋቢው የአልፋሽቃ አከባቢ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንደቀጠሉ ሲሆን ቦታው የሁለቱ ሀገራትን የጋራ ድንበር የሚያገናኝ ነው። ኢትዮጵያውያን አከባቢውን ማዘጋ በሚል የሚጠሩት ሲሆን የትግራይ ጦርነት እስከተጀመረበት ጥቅምት 2020 ድረስ በአማራ ክልል አስተዳደር ስር ነበር።

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.