ዜና፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፌዴራል ፖሊስ አባላት ከመኖሪያ ቤቱ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20/2015 ዓ.ም፡- “ፍትሕ” መጽሔት መስራች እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ጠዋት ከመኖሪያ ቤቱ መወሰዱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፀ፡፡

የፌዴራል ደምብ ልብስ የለበሱ እና ሲቪል የለበሱ በሁለት ፓትሮል የታጀቡ የፀጥታ አካላት ጠዋት 12፡ 30 ላይ ወደ መኖሪያ ቤቱ በማምራት ተመስገን ደሳለኝን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የገለፀው ወንድሙ ወዴት እንደተወሰደም ቤተሰቦቹ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን ተናግሯል፡፡

ታሪኩ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍርድ ቤት ክስ እንደሌለበት ገልፆ በቅርቡ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ቢሮ ወስደውት ለትንሽ ሰዓታት ካቆዩት በኋላ ሰኞ እንፈልግሃለን ብለው ለቀውት ሰኞ ተመልሶ ሄዶ ሲጠይቅ ለምን እንደፈለግንህ አጣርተን እንነግርሃለን ብለው እንደመለሱት ጠቅሷል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.