አዲስ አበባ፣ ጥር 19/ 2015 ዓ.ም፡- የ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከተፈተኑት አጠቃላይ 896 ሺ 520 ተማሪዎች ውስጥ 50 በመቶ እና በላይ ያመጡ ተፈታኞች 29,909 (3.3በመቶ) ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የተመዘገበውን ውጤትም “አስደንጋጭ” ብሎታል፡፡
የትምህርት ሚንቴሩ ፐሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከሰዓት ለሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከአጠቃላይ ከተመዘገቡ 985,384 ተማሪዎች 77,098 የሚሆኑት ፈተናውን የልተፈተኑ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 20ሺ 170 ተማሪዎች በግል ደንብ ጥሰት፣ በቡድን ለመፈተን በመሞከራቸው በተወሰደ እርምጃ እንዲሁም የተወሰኑት ፈተናውን ጥለው በመሄዳቸው ፈተናውን አለመውሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡
አክለውም በፈተናው ውጤት 50በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግባት እንደማይችሉ የገለፁ ሲሆን ነገር ግን ወደ አማካዩ (50በመቶ) የሚጠጋ ውጤት ላስመዘገቡ 100 ሺ ለሚሆኑ ተማሪዎች ለዚህ አመት ብቻ በመደበኛ ተማሪ ሳይደረጉ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡበትን ትምህርት አይነት ተምረው ፈተና ወስደው ካለፉ የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንዲሆኑ ይደረጋሉ ብለዋል።
ይህም የተደረገው ክህሎት ያላቸውን ተማሪዎች ላለማጥት እድል መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ የተቀሩት ግን ቴክኒክ እና ሙያ ትምህት ቦቶች ገብተው መማር ይችላሉ ነው ያሉት፡፡
የዘንድሮው ውጤት እጅግ አስደንጋጭ ነው ያሉት ሚንስትሩ ለዚህም ተጠያቂዎቹ “መንግስት፣ ተማሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ መምህራን እንዲሁም ወላጆች” መሆናቸውን ገልፀው በውጤቱ የወደቁት ተማሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ሀገሪቱ የትምህርት ስርዓትም መውደቁን ያሳያል ብለዋል፡፡
በፈተናው የተሻለ ውጤት የተመዘገበው በአዲስ አበባ፣ ሀረር እና ድሬ ደዋ ሲሆን በተቀሩት ክልሎች ተቀራራቡ የሆነ ዝቅተኛ ውጤት መመዝገቡን ሚንስትሩ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከተፈጥሮ ሳይንክ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 666 (ከ700) ሲሆን ከማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 524 (ከ600) መሆኑም ተገልጧል፡፡
ምንም እንኳ በዛሬው መግለጫ ሚንስቴሩ ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሰጠቱ የሀገሪቱን የትምህርት ችግር እንድናውቅ ማስቻሉንና የትምህርት ጥራትን ለማሸሻል የሚረዳ መሆኑን እንዲሁም የፈተና ስርቆትን ሙሉ በሙሉ መስቀረት በመቻሉ ስኬታማ መሆኑን ቢገልፁም በፈተናው ወቅት ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ በፈጠሩት ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉንና በፈተና አስፈጻሚዎችና በፀጥታ ሃይል ላይ ጉዳት መድረሱን ይታወቃል፡፡
ፈተናው ከመሰጠቱ ቀደም ብሎ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው ተማሪዎቹ ፈተናውን ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በዩኒቨርሲቲዎች እንዲወስዱ መደረጉ ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ገልፀው ነበር፡፡ አስ