ዜና፡ የፑንትላንድ ፖሊስ ኢትዮጵያ የተወለደ የዳየሽ ታጣቂ  መሪን  መግደሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5/2015 ዓ.ም፡- የፑንትላንድ መንግስት ፖሊስ ባወጣው መግለጫ፣ የፀጥታ ሃይሎች ጥር 2 ባካሄዱት ዘመቻ ኢትዮጵያ የተወለደ የዳየሽ ታጣቂ ቡድን መሪ አቡ-አልባራ አል አማኒን መግደላቸውን አስታወቀ፡፡

የፑንትላንድ መንግስት የቴሌቨዥን እንደዘገበው፣ ታጣቂዎቱ በባሪ ክልል ባሊ-ዲዲን ወረዳ ላይ ለመፈፀም ያቀዱትን ጥቃት የፑንትላንድ ፀጥታ ሀይሎች መከላከል ችለዋል።

የቴሌቨዥን ጣቢያው የፑንትላንድ ፖሊስ አዛዥን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በዳየሽ ታጣቂዎች የዳየሽ ኦፕሬሽን ኃላፊ ሆኖ የተሾመው አቡ-አልባራ አል አማኒ የተገደለው በካልሚካድ ተራሮች አካባቢ የፑንትላንድ የጸጥታ ሀይሎች ከታጣቂው ቡድን ጋር ባደረጉት ጦርነት ነው።

ኣይ.ኤስ.አይ.ኤስ( ISIS) በመባል የሚታወቀው የዳየሽ ታጣቂ ቡድን በአለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት የተፈረጀ ቡድን ነው።  ቡድኑ እ.አ.አ ሚያዝያ 2015 ሊቢያ ውስጥ 28  ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን አሰቃቂ በሆነ መልኩ አንገታቸውን መቅላታቸው ይታወቃል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.