ዜና፡ የአማራ ልዩ ሀይል ከሽረ እና ከአካባባው መውጣቱን መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5/ 2015 ዓ.ም፡- መከላከያ ሰራዊት ትላንት ባወጣው መግለጫ ከመቀሌ 140 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ  ከምትገኛው ሽረ እና አካባቢው የነበሩ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ለቀው መውጣታቸውን አስታወቀ፡፡

መከላከያ ሰራዊት  እንዳስታወቀው ልዩ ሀይሉ ቀጠናውን ለቆ የወጣው በፌዴራል መንግስትና በህወሃት አመራሮች መካከል በደቡብ አፍሪካና በኬኒያ የተደረሰውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ ነው።

ይህ የተከናወነው ጥር 2 በአፍሪቃ ኅብረት ታዛቢ እና አረካካቢ ኮሚቴ አባላት የትግራይ ሃይሎች ትጥቅ የማስፈታት ሂደት መጀመሩን እና ከባድ መሳርያ ለመከላክያ ሰራዊት ማስረከባቸው መግለፃቸውን ተከትሎ ነው፡፡

የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ በተገኙበት በስፍራው የታየው የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ለቆ እንዲወጣ ተደርጓል። ጄኔራሉ በመንግስት በተላለፈው ትዕዛዝ መሠረት በተደረሰው የሠላም ስምምነት ሃይሉ ከአካባቢው እየወጣ ነው ብለዋል።

ነገር ግን የትግራይ ሃይሎች ትጥቅ የማስፈታት ሂደትን እና  ከባድ መሳርያ ማስረከባቸውን የገለፁት የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም ስምምነቱ ቁጥጥር ኮሚቴ አባላት፣ የአማራ ልዩ ሃይል ከቀጠናው የመውጣቱን መረጃ  አላጋሩም፡፡

ህዳር 3 ቀን በናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት በፕሪቶርያ የተደረሰው ስምምነት መሰረት “የትግራይ ሃይሎች ትጥቅ የማስፈታት ተግባር ተፈጻሚ የሚያደርገው በአንቀጽ 2.1/D ስር “የከባድ መሳርያ ትጥቅ ማስረከብ የውጭ ሃይሎችና ከኢትዮጵያ መከላክያ ውጭ የሆኑት ታጣቂዎች ከክልሉ ሲወጡ እንደሆነ” ተገልጿል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.