አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10/ 2015 ዓ.ም:- የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በትናንትናው እለት ለክልሉ ሚዲያ፣ የፕሪቶሪያ እና የናይሮቢ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ በእነሱ በክል ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን ገልፀው የኢትዮጵያ መንግስት ግን የስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ወደ ኋላ ቀርቷል እሉ፡፡ ደብረጽዮን ይህን ያሉት ከትግራይ ክልል ምክር ቤት አባላት ጋር ትላንት ባደረጉት ውይይት ላይ መሆኑን የክልሉ ሚድያ ገልጧል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት የፌደራል መንግስት ቅዳሜ እለ፤ በትግራይ ክልል ውስጥ መቐለ ከተማን ጨምሮ በክልሉ “የተደራጁ ወንጀሎች” በመበረከታቸው ንጹሃን ዜጎችን ለመጠበቅ “አርምጃ እወስዳለው” የሚል መግለጫ መስጠቱን ተከትሎ ነው።
“የአገር መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ባልደረሰባቸው አካባቢዎች የተደራጁ ወንጀሎች እየተፈፀሙ እንደሆነ ተገልጧል። “እነዚህ ወንጀለኞች የሽግግር ሁኔታውን እንደ አንድ መጠቀሚያ አድርገውታል ያለው የፌደራል መንግስት መግለጫው በተለይም በመቐለ ከተማ፣ በታጣቂ ፓትሮል ታጅበው የተደራጀ ዘረፋ እየተፈፀመ መሆኑን የሚገልጹ ሪፖርቶች እየወጡ ነው ብሏል፡፡
የፌደራል መንግስት “በእነዚያ አካባቢዎች የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ እና ኃላፊነቱን ለመወጣት አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ ይወስዳል” ሲል መግለጫው አክሎ ገልጧል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የትግራይ ክልል ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም። ሆኖም የሕወሃት ቃል አቀባይ እና የትግራይ ማዕከላዊ ዕዝ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገፃቸው “ እኛም ሆን ህዝባችን ልንፈታው ያልቻለውን የትኛውንም የፀጥታ ችግር ማንም ሊፈታው አይችልም” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ገልፀዋል።
የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ደብረጽዮን እሁዱ እለት ከክልሉ ምክር ቤት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የትግራይ ሃይሎች ከአራት ጦር ግንባሮች መውጣታቸው ያስታወቁ ሲሆን የመንግስት ሃይሎች ግን ተመሳሳይ ተግባር አልፈጸሙም ብለዋል።
የፌደራል መንግስት በደብረፂዮን መግለጫ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። አስ