ዜና፡ የጋራ ግብረ ሃይሉ በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች ላይ ወሳኝ እርምጃ እየወሰድኩ ነው ሲል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች ላይ ወሳኝ እርምጃ እየወሰድኩ ነው ሲል ገልጿል። በአማራ ክልል ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር የሚንቀሳቀሱ ሀየሎች አሉ ሲል ኮንኗል። ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን በሚል በውስጥም በውጭም በመቀናጀት የራሳቸውን ህቡዕ አደረጃጀት የፈጠሩ አካላት ከመሰል ቡድኖች ጋር በመቀናጀት የሕዝቡን የቁርጥ ቀን ልጆች መልሰው እየበሉ ነው ሲል የግብረ ሀይሉ በመግለጫው ማመላከቱን በሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በዘገባዎቻቸው አስታውቀዋል።

የግብረ ሀይሊ መግለጫ የወጣው የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ እና የግል ጥበቃዎቻቸው ሰሜን ሸዋ ዞን ከመሀል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሀን ሲመለሱ ልዩ ቦታው መንዝ ጓሳ አካባቢ በታጠቁ ሃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ነው።

እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች በትናንትናው ዕለትም የአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕት ቤት ኃላፊ እና የክልሉ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን ግርማ የሺጥላን በመግደል አስነዋሪ ድርጊታቸውን አስመስክረዋል ሲል መግለጫው ማመላከቱን ዘገባዎቹ አካተዋል።

የጋራ ግብረ ሃይሉ በስም ያልጠቀሳቸው ቡድኖች በህቡዕ ተደራጅተውና ተቀናጅተው ሕገ ወጥ ተግባራቸውን ቀጥለዋል ሲል መኮንኑን እና በየአካባቢው የተደረጉ የሽምግልና ሂደቶችን መግፋታቸውን እንዲሁም የተቀበሉ በመምሰል በክልል በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን አስታውቋል።

ምን አይነት እርምጃዎች መወሰዳቸውን ያልጠቀሰው መግለጫው አስፈላጊና ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቆ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በቀጣይ ለሕዝቡ የማሳወቅ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁሟል። በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ከሚተላለፉ ያልተረጋገጡ ወሬዎች  ሕብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ ግብረ ሀይሉ ማሳሰቡን ዘገባዎቹ አመላክተዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.