ዜና፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እየተወያየ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3/ 2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፓትሪያርኩን ጨምሮ  አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር በጠቅላይ ሚንስትሩ ጵ/ቤት እየተወያዩ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ወይይቱ እየተደረገ ያለው የኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ትላንት ባወጣው መግለጫ ላይ የቤተ ክስቲያኒቱን ሃይማኖት ቀኖና እና አስተዳራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ  ከመንግስት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በገለፀችው መሰረት ጠቅላይ ሚንስትሩ ለውይይት ጥሪ በማቅረባቸው መሆኑንን የሲኖዶሱ መግለጫ ገልጧል፡፡

 “ወይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሊሆን የሚገባ ነው በሚል በተነሳው ሐሳብ በጉዳዩ ላይ ከሽማግሌዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ የደህንነት ተሽከካሪዎች እና የጸጥታ አባላት ብዛት ሲታይ ምእናንን ስጋት ላይ እንዳይወድቁ እና ለልተገባ ጉዳት እንዳይዳረጉ በማሰብ የሰላም ጥሪውን መንግስት ከተቀበለ እና በቤተ መንግስት መገኘቱ ለሕዝባችን የሚያመጣው መፍትሄ የሚኖር እንደሆነ በመሳብ ፓትሪያርኩን ጨምሮ  አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግስት እየተወያዩ” መሆኑ ተገልጧል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ በመግለጫው ህዝበ ክርስቲያቡ ውጤቱን በትእግስት እንዲጠባበቅ  አሳስቧል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.