ዜና፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር አነሳ

ፎቶ ከፋይል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13/ 2015 ዓ.ም – የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ህወሓትን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ማንሳቱ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ከኦነግ ሽኔ (የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኘውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን መንግስት የሰጠው ስያሜ) ጋር በሽብርተኝነት የፈረጃቸው ከሁለት አመታት በፊት ሚያዚያ ወር ላይ ነበር።

በተመሳሳይ በፓርቲው ሊቀመንበር ስም በሚጠራ መዝገብ አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የፌደራል አቃቤ ህግ 62 የሚሆኑ የቀድሞ እና በስልጣን ላይ ያሉ የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የሽብር ክስ መመስረቱ ይታወሳል። ህወሓት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲነሳ የተደረገው የሰላም ስምምነቱ ይበልጥ መተማመን እንዲፈጥር ለማስቻል መሆኑ ተጠቁሟል። አለማቀፉ ማህበረሰብ በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል በሚል ህወሓት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲያነሳ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ እንደነበር ይታወሳል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.