ዜና፡ የአፍሪካ ህብረት በትግራይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን ምርመራ ግልጽ ባልሆነ መንገድ አቆመ፤ ህብረቱ በድረገጹ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ የሚሰጠውን ገጽ አስወግዶታል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5/2015 ዓ.ም፡- የአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን እንዲመርመር ያቋቋመውን ኮሚሽን ይፋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲቆም ማድረጉ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ለሁለት አመታት የታካሄደውን ጦርነት ተከትሎ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር የተቋቋመ የመጀመሪያው ኮሚሽን መሆኑ ይታወሳል።

ምርመራው እንዲቋረጥ ከማድረጉ በተጨማሪ የህብረቱ ኮሚሽን በድረገጹ የነበረውን እና  በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ የሚሰጠውን ገጽ እንዳስወገደው ታውቋል።

ህብረቱ በትግራይ ሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ምርመራ እንዲያካሂድ ያቋቋመውን ኮሚሽን ስልጣኑ እንዲያበቃ እና የሚያካሂደው ምርመራ እንዲቋረጥ ውሳኔ ያሳለፈው ከአንድ ወር በፊት መሆኑም ተጠቁሟል። ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጀምሮ ይፋ ያደረገው ሪፖርት የለም።

በትግራይ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ ህብረቱ ኮሚሽኑን ያቋቋመው ከሁለት አመት በፊት መሆኑ ይታወሳል። በወቅቱም የኮሚሽኑን መቋቋም የኢትዮጵያ መንግስት አንደተቃወመው በይፋ አስታውቆ ነበር። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.