የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት ፋንቱ ደምሴ ፡ ፎቶ- አዲስ ስታንዳርድ አፋን ኦሮሞ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23/ 2015 ዓ.ም፡- የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ማንነት እውነት እንዲወጣ ባለቤቱ ፋንቱ ደሚሴ ትላንት ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው ሁለተኛው የሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ መርሃ-ግብር ላይ በደረገችው ንግግር ጠየቀች፡፡ የአርቲስቱ ባለቤትና የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ሰብሳቢ ፋንቱ ሶስት አመት ሙሉ የሀጫሉን ግድያ ፍትህ አላየሁም፣ እውነቱ እስካልወጣ ድረስ ለእኔ ማንም ንፁህ አይደለም ስትል ገልፃለት፡፡
ለአሸናፊ አርቲስቶችና የኪነጥበቡ ባለሙያዎች ሽልማትና እውቅና በተሰጠበት መርሃ-ግብር ባደረገችው ንግግር፣ “ ጥለሀን ከሄድክ በኋላ እውነት ላይ ተኝተው እኛ እንዳለን አለን፣ የበላህም ያስበላህም ዘመድ ይሁን ጠላት ሳናውቅ አለን፣ የሃገራችን ነገር አለባብሶ ማለፍ ነው” ስትል ተናግራለች፡፡
ሀጫሉ የሚገባው ሽኝት መከልከሉን ያስታወሰችው ፋንቱ “እውነቱ እስካልወጣ ድረስ ለእኔ ማንም ንፁህ አይደለም፣ አሁንም ቢሆን እውነቱን እንድታወጡ እጠይቃችኋለው” በማለት ከግድያው ጋር ያለው እውነት እንዲወጣ ጠይቃለች፡፡
በመጨረሻም በአካል ከተለየከን ቀን ጀምሮ እኔ እና ልጆችህ ከአንተ ናፍቆት በቀር እውነትንና የሰውን ደም የምትመጥ ሀገር ላይ ሆነን ሶስት አመት ሞላን ስትል ተደምጣለች፡፡
በሽልማት በርሀ-ግብሩም አቡበከር ሙሳ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆነው ተሸልመዋል፡፡ በአርቲስቶች በኩል ሽመልስ አለሙና ቲሉ ወሌ “ዳዶ በሚል ዘፈን የአመቱ ምርጥ ኬሮግራፈር ዘርፍ ተሸላሚ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ሊዮስ ዋሎ አባ ቦቲ በሚል ዘፈን የምርጥ ኤዲተር ዘርፍ ተሸላሚ ሲሆን ብሩክ ግርማ ከን ጂዲን በሚል ዘፍኑ ምርጥ ቪዲዮ ክሊፕ ተሸላሚ ሆኗል፡፡አስ