አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4/ 2015 ዓ.ም፡- የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር መልካሙ ሹምዬ በገዛ ፍቃዳቸው ከድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርነት እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡
ምክትል ሊቀመንበሩ ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በፃፉት ደብዳቤ ኃላፊነታቸውን ለመልቀቃቸው ከአብላጫ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ያላቸው የአቋም ልዩነት እየሰፋ መሄዱ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ መልካሙ በስራ አስፈፀፃሚው ኮሚቴው ውስጥ አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር እና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ መቀጠል የድርጅቱንና የህዝቡን ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ ባለማግኘቴ ኃላፊነቴን ለመልቀቅ ወስኛለው ሲሉ በደብዳቤያቸው አስታውቀዋል፡፡ ነገር ግን በፓርቲው ውስጥ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል፡፡ አስ