አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29/ 2015 ዓ.ም ፡- የነቀምት ከተማ ከንቲባ አቶ ቶሌራ ረጋሳን ጨምሮ በርካታ የከተማዋ ባለስልጣናት ከነቀምት ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ ግድያ ጋር በተያያዘ ለእስር መዳረጋቸው ተገለጸ።
የነቀምት ከተማ የብልጽግና ሃላፊ ከሳምንት በፊት ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን ተክትሎ ከንቲባ ቶሌራ ረጋስ የታሰሩት መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሆነ እና ፍርድ አለመቅረባቸውን የከንቲባው ባለቤት እጅጋየሁ አምባራስ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል። ከከንቲባው ጋር በግድያው ተጠርጥረው የታሰሩ ሌሎች አስራ አንድ ባለስልጣናት በትላንትናው እለት ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር ባለቤታቸው እጅጋየሁ መናገራቸውን ዘገባው አካቷል።
የከተማዋ የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ ደሳለኝ በኮንጃ በተገደሉ ማግስት ከንቲባው መታሰራቸውን የጠቆመው ዘገባው አቶ ደሳለኝ በመኖሪያቸው ደጃፍ ላይ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።
እጅጋየሁ ለደህንነታቸው ሲሉ ልጆቻቸውን ይዘው በሌላ ከተማ እንደሚኖሩ ያስታወቀው ዘገባው ባለቤታቸው ከታሰሩ ጀምሮ ማግኘት አለመቻላቸውን እና ለምን እንደታሰሩ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን አካቷል። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የከተማው አስተዳደር ባልደረባ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ እንዳስታወቁት ከንቲባው እና ሌሎች የከተማዋ ባለስልጣናት ከሹፌሮቻቸው እና የግል ጠባቂዎቻቸው ጋር ከብልጽግና ሃላፊ ግድያ ጋር ተጠርጥረው መታሰራቸውን አመላክተዋል። የከተማዋ አስተዳደር እና የክልሉን ባለስልጣናት መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ዘገባ አስታውቋል። አስ