ዜና፡ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ከሰኔ ሰላሳ አስቀድመው ወደ ቤታቸው እንዲገቡ አሳሰበ

አቶ ሽመልስ ታምራት

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17/2015 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ዕጣ በደረሳቸው የጋራ መኖሪያ ቤት መግባት እንደሚጠበቅባቸው በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የውሃ፣ የመብራትና መንገድን ጨምሮ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን አስቀድሞ ለሟሟላት የከተማው ቤቶች ልማት ቢሮ እና ኮርፖሬሽኑ ከመሰረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም ዋና ዳይሬክቴሩ አቶ ሽመልስ ተናግረዋል ።

ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን በሚፈለገው ደረጃ ለማሟላት ዕጣ በወጣባቸው 32 ሳይቶች ከሰኔ ሰላሳ በፊት ለማሟላት ከመሰረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር የስራ ሰዓት ማሻሻያን በማድረግ፥ ስራዎችን ማፋጠንን ጨምሮ የአፈጻጸም ክትትል በማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው አስረድተዋል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ዘግቧል።

በዚህም መሠረት ዕድለኞች ከሰኔ ሰላሳ በፊት አስቀድመው መግባት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ቀሪ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለሟሟላት ከመሰረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አመላክተዋል።

ቀበሌ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎችንም የመንግስት ቤቶችን ይዘው የተቀመጡ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ቤቶቹን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ማስተላለፍ እንዲቻል ከሰኔ ሰላሳ አስቀድመው መልቀቅ እንደሚጠበቅባቸው ገልፁዋል።

የቤት ዕድለኞቹ የአካባቢ ጽዳትና ውበት ስራን ጨምሮ የጸጥታ ስራዎችን በአካባቢው ከሚገኙ የጸጥታ ተቋማት ጋር መከወን እንዲቻል አስቀድመው መግባት ይጠበቅባቸዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.