ዜና፡ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሃላፊ ከስራ መሰናበታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም፡- የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶውሳ ከኩባንያው መሰናበታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ያገኘው መረጃ አመላክቷል። ሃላፊው ለሁለት አመታት ያክል በኢትዮጵያ የኩባንያው ዋና ሃላፊ ሁነው ማገልገላቸው ይታወቃል።

አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው የውስጥ ማስታወሻ እንደሚያመለክተው በቀጣይ ወር ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ የስራ ግዜያቸው ሲጠናቀቅ ከኩባንያውን የኢትዮጵያ ሃላፊነታቸው እንደሚሰናበቱ ተገልጿል።

ኩባንያው አንዋር ሶውሳን በኢትዮጵያ በዋና ስራ አስፈጻሚነት ደረጃ እንዲያገለግሎ ሾሟቸው የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ሳፋሪኮም አራት ሚሊየን ደንበኞችን እንዲያፈራ ማስቻላቸውን እና አገልግሎቱም 25 በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ህዝብ ያክል ሽፋን እንዲያገኝ ማድረጋቸውን ጠቅሶ ኩባንያው እንዳወደሳቸው የውስጥ ማስታወሻው ላይ ተመላክቷል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.