አዲስ አበባ፣ ጥር 5/ 2015 ዓ.ም፡- የሰብዓዊ መብት ተማጓቹ ሂዩማን ራይትስ ዎች የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የሽግግር ፍትህን እንዲኖር በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተፋላሚ ወገኖች ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጠየቀ።
የ2023 ሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት በአለም ዙርያ አመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን የገመገመ ሲሆን፣ “ምንም እንኳን በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ግጭት ለሁለት ዓመታት በተዋጊ ወገኖች ብዙ የጅምላ ግድያን ያደረሰ ቢሆንም ዩክሬን ካገኘችውን ዓለም አቀፋዊ ትኩረት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ጥቂት ብቻ ነው ” ብሏል፡፡
አክሎም በምእራብ ትግራይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በርካታ ሞት፣ የፆታ ጥቃት፣ የጅምላ እስር እና በሺዎች የሚቆጠሩ መፈናቀልን አስከትሏል ብሏል፡፡
በተጨማሪም 2022 የዘለቀው የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል ላይ ያደረገው ከበባ ንፅሃን ዜጎች የምግብ፣ የመድሃኒት እና የህይወት አድን ሰብአዊ ርዳታ እንዲሁም የመብራት፣ የባንክ እና የኮሙኒኬሽን አገልግሎትን እንዳያጉኙ ማድረጉ የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ብላሏል፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ህብረትን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን እና አሜሪካን ጨምሮ አለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ ከባድ ወንጀሎችን የፈፀሙ በህግ እንዲጠየቁ በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ ተፋላሚ አካላቱ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ አሳስቧል። “መንግሥታት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግድያውን፣ ሰፊውን ፆታዊ ጥቃት እና ዘረፋ ቢያወግዝም የወሰዱት እርምጃ የለም” ብሏል።
በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ያለውን ቀውስን በተመለከተ፣ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎችና ታጣቂዎች በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የመብት ጥሰት የፈፀሙ ሲሆን፣ ግጭቶችና ሁከቶችም በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎችም ተከስተዋል ያለው የመብት ተማጓቹ፣ በድርቁ ምክንያት ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲሹ ምክንያት ሆኗል ብሏል፡፡
“በምእራብ ኦሮሚያ በመንግስት እና በታጠቁ አካላት መካከል የነበረው ግጭት በሁለቱም ወገን ከፍተኛ የህግ ጥሰጥ ተፈፅሟል” ነው ያለው ሂዩማን ራይትስ ዎች፡፡
ሪፖረቱ፣ በሰሜን ኢትዮጵያም ሆነ በኦሮሚያ በተፋላሚ ወገኖች የተፈፀሙ የአለማቀፋዊ ህግ ጥሰቶች መረጃዎች እየጨመሩ ቢሄዱም መንግስት ከዚህ ቀደምም ሆነ በአሁኑ ወቅት ለተፈፀመው የመብት ጥሰት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት በቂ እንዳልነበር፣ ግልጽነት የጎደለው እና ገለልተኛ ክትትል እንዳልነበረው በአፅንዖት ገልጧል።
በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለአሰቃቂ ጥቃጦች በመዳረግ እጅግ አስከፊ የሰበዓዊ መብት ጥሰት እየተባባሰ መጥቷል፡፡አስ