ዜና፡ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ የነበሩትን ጨምሮ አምስት አመራሮች በህግ እየተፈለጉ መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19/2015 ዓ.ም፡- የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ የነበረችውን ሀቢባ ኡመርን ጨምሮ የክፍለ ከተማው አምስት አመራሮች በህግ እየተፈለጉ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ  አሳወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለጸው ሃላፊዋን ሀቢባ ኡመርን ጨምሮ ምክትል ሃላፊው ተስፋዬ ግርማ፣ የመሬት አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት በቃሉ ጸደቅ እና ጨምዴሳ ፉለአ እንዲሁም በክፍለ ከተማው የወረዳ አራት አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበረው ልዑል ተረፈ በህግ እየተፈለጉ ነው ተብሏል።

ግለሰቦቹ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም፣ ሃሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው የመንግስት እና የህዝብ መሬት እንዲመዘበር በማድረጋቸው በተጠረጠሩበት ወንጀል እየተፈለጉ መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስም ተጠርጣሪዎቹ ያሉበትን ህብረተሰቡ እንዲጠቁም ጥሪ አቅርቧል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.