ዜና፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት እና ወ/ሮ ዘሃራ ኡመር የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዜዳንት አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26/2015 ዓ.ም፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ በሚገኘው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሹመትን አፅድቋል፡፡

በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትነት በእጩነት ያቀረቧቸው ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት ሆነው ተሸመዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሹመትን በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያፀደቀው።

በተጨማሪም ወ/ሮ ዘሃራ ኡመር የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው የተሸሙ ሲሆን ምክር ቤቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሹመትን በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

ይህ አዲስ ሹመት የተሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንት ከሁለት ሳምንታት  በፊት  ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው በመልቀቃቸው ነው፡፡

ፕሬዚደንት የነበሩት አቶ ብርሃነመስቀል ዋጋሪና ምክትል ፕሬዚደንቷ  ወ/ሮ ተናኘ ጥላሁን ላለፉት ሦስት ዓመታት አገልግለዋል። ፍርድ ቤቱ ሁለት ምክትል ፕሬዚደንቶች ያሉት ሲሆን ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው እያገለገሉ ያሉት አቶ ተኽሊት ይመስል ናቸው። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.