ዜና፡ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳርን እንዲመሩ መረጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9/ 2015 ዓ.ም:- የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮምቴ ትላንት ማምሻውን የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳን የክልሉ ግዜያዊ አስተዳደር እንዲመሩ መምረጣቸውን ሶስት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

አቶ ጌታቸው ረዳ ከ41 የማዕከላዊ ኮምቴ አባላት 18 የድምጽ ብልጫ አግኝተው መመረጣቸውን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል።

የተቋቋመው ግዜያዊ አስተዳደር ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የተመረጠውን የትግራይ ክልላዊ መንግስትን የሚተካ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ጥቅምት 23 ቀን 2015ዓ/ም ከፌደራል መንግስት ጋር  በተደረገው ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ዋና ከሆኑ ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ የሰላም ስምምነቱ ሰነድ አንቀጽ 10 አካታች ግዜያዊ አስተዳደር መመስረት አንዳለበት ይደነግጋል።

የትግራይ ክልል መስተዳድር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር)የክልሉ ምክር ቤት ምርጫን ተከትሎ በክልሉ ፓርላማ በከፍተኛ ድምጽና ድጋፍ ለፕሬዝዳንትነት ተመርጠው  የነበረ ቢሆንም የፌደራል መንግስት ከህግ ውጭ ነው በሚል ውድቅ አድርጎት ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዶ/ር ደብረፂዮን በአመራርነታቸው እንዲቀጥሉ ህወሓት ያቀረቡትን ሃሳብ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ማዕከላዊ ኮሚቴው የድርድሩ ቡድን አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳን ለመምረጥ አዲስ ምርጫ አንዲካሄድ ወስኖ መመረጣቸው ምጮቹ ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን የፌደራል መንግስት ይሁኝታ ይሰጠው እንደሆነ ገና የሚታይ ነው።

በመቐለ ዩንቨርስቲ የህግ መምህር የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ከኢህአዴግ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አንዱ የነበሩ ሲሆን፤  የፌደራል መንግስት የኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር በመሆንም ጭምር አገልግለዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.