ዜና፡ የሀገሬ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አድማሱ በጸጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14/2015 ዓ.ም፡- የሀገሬ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ ብርሃኑ አድማሱ ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት አራት ሰዓት አከባቢ የፌደራል ፖሊስ መለያ የለበሱ የጸጥታ ሀይሎች ለጥያቄ ትፈለጋል በሚል እንደወሰዷቸው አዲስ ስታንዳርድ ከቴሌቪዥን ጣቢያው ሰራተኞች አረጋግጣለች።

በፓትሮል የመጡ የጸጥታ ሀይሎች ስራ አስኪያጁን ቢሮ ድረስ በመግባት እንዳነጋገሯቸው እና ይዘዋቸው እንደሄዱ ባልደረቦቻቸው ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል። ለጥያቄ ትፈለጋለህ ከማለት ውጪ የተነገራቸው ዝርዝር ነገር እንደሌለ የቴሌቪዥን ጣቢያው ሰራተኞች ገልጸዋል።

የሀገሬ ቴሌቪዥን ጣቢያ በይፋ ስርጭት ከጀመረ ከሁለት አመት በላይ እንደሆነው የጣቢያው ሰራተኞች አስታውቀዋል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.