በኢትዮጵያ የኮቪድ የጤና ባለሙያዎች፤ ፎቶ፡ የአለም ጤና ድርጅት/ከክምችት
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17/ 2015 ዓ.ም፡- የከቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ በሽታውን ለመከላከል በተደረገው ጥረት በጤና ሚኒስቴር በቀረበላቸው ጥሪ መሰረት ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በኮንትራት ሲያገለግሉ የነበሩ 3 መቶ 40 የጤና ባለሙያዎች በቋሚ እንዲስተካከልላቸው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን መመሪያ ያወጣ ቢሆንመ መመሪያውን በመተላለፍ ከስራ እንድንለቅ ተደርገናል ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ቅሬታ አቀረቡ፡፡
የጤና ባለሙያዎቹ ለጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት እና ለሌሌች ጉዳይ ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ የፃፉ ሲሆን በደብዳቤውም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከሃምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ቋሚ እንድንሆን ተብሎ ተወስኖ፣ በርካቶች የእድሉ ተጠቃሚ ቢሆኑም እኛ ግን ከስራ እንድንለቅ ተነግሮናል ብለዋል፡፡
ጤና ሚኒስቴር ከሲቪል ሰረቪስ ኮሚሽን በተፃፃፈው እና ሌሎች ጤና ባለሙያዎችን ቋሚ ባደረገበት መመሪያ መሰረት ቋማ እንደሚያደርጉን እየነገሩን ለዚህም ለኮንትራት ተቀጣሪ ተብሎ 50% ጭማሪ የተደረገው ወደ ቋሚነት እየዞራችሁ ስለሆነ በሚል ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እንደተቀነሰባቸውም አስፍረዋል፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በየስድስት ወር በሚታደስ ኮንትራት ለሶስት ዓመታ ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በእጃችሁ ያለን የመንግስት ንብረት አስረክበው እንዲወጡ እንደተነገራቸው በደብዳቤው አስፍረዋል፡፡ መፍትሄ እንዲሰጠን ሚኒስትር መስሪያ ቤቱን ብንጠይቅም መፍትሄ ማግኘት አልቻልንም ያሉት ባለሙያዎቹ “እርምጃ የተወሰደው ቦታና በጀት ስለሌለ ነው” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው በደብዳቤያቸው አክለው ገልፀዋል፡፡
ከቅሬታ አቅራቢዎች መካከል አንድ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ የጤና ባለሙያ በጤና ሚንስቴር በኩል በተደረገልን ጥሪ መሰረት በኮንትራት ስናገለግል የቆየን ሲሆን ሐምሌ 2013 ዓ.ም. ቋሚ እንደምንደረግ በደብዳቤ ተነግሮን፣ እስከ 80 በመቶ የሚሆኑትን ባለሙያዎች ብቻ ቋሚ አድረገው ቀሪዎቻችንን ትተውናል ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጧል፡፡
አስተያየት ሰጪው አያይዞም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቋሚ ትሆናላችሁ የሚል ደብዳቤ ቀድሞ ሰጥቶን የነበረ ቢሆንም ከታህሳስ 30 በኋላ የኮንትራት ግዚያችን ማብቃቱ ተገነግሮናል ብሏል፡፡
የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ደኤታ ዶክተር አየለ ተሾም የጤና ባለሙያዎቹ በሚሰሩበት የጤና ተቋም አቅም በፈቀደ መጠን ቋሚ እንዲሆኑ ሲቪል ሰርቪስ መፍቀዱን ገልጠው ከ5ሺ በላይ የጤና ባለሙዎች ቋሚ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
ሚንስትር ደኤታው ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት በኮንትራት ግዚያቸው አፈፃፀም ላይ ጉድለት የታየባቸው እና የስነ-ምግባር ጉድለት የተስተዋለባቸው አንዳንድ ባለሙያዎችን ግን ተቋማቱ ቋሚ አላደረጉም ብለዋል፡፡ አክለውም የባለሙያዎቹን ክፍያ የሚፈፅመው የጤና ሚንስቴር መሆኑን ጠቅሰው ለኮቪድ 19 ወረርሺኝ የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ በመቆሙ የባለሙያዎቹን ኮንትራት ማደስም ሆነ ቋሚ ማድረግ አቅም እንደሌለ ገልፀዋል፡፡
ከመብታቸው አንፃር የተነካ መብት የለም ያሉት ዶ/ር አየል የጤና ተቋማቱ ባለሙያዎቹን ቋሚ ሲያደርጉ ክፍተት አለ ብለው ያሚያስቡ ከሆነ ተቋማቱን በህግ መጠየቅ ይችላሉ ብለዋል፡፡ አስ