ዜና፡ ከእስር ለማምለጥ በደቡብ ክልል በፖሊሶች አይን ላይ ሚጥሚጣ የበተኑ ከአራት ታራሚዎች ውስጥ ሁለቱ  አመለጡ፤ የአንድ ታራሚ ህይወት አልፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር፣ 4/ 2015 .ም፡ ከሀላባ ማረሚያ ተቋም ወደ ወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ አራት ተከሳሽ የህግ ታራሚዎች ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ መጡበት ሲመለሱ መንገድ ላይ በማረሚያ አጃቢ ፖሊሶች አይን ሚጥሚጣ በመበተን ለማምለጥ ባደረጉት ሙከራ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት የአንድ ታራሚ ህይወት ሲያልፍ ሁለት ታራሚዎች ማምለጣቸዉ ተገለፀ፡፡

ህይወቱ ካለፈ አንዱ ታራሚ በተጨማሪ ሌላ አንድ ታራሚ በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ቆስሎ መያዙን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሸን  አስታዉቋል

ህይወቱ ያለፈዉ የህግ ታራሚ እና የቆሰለው ግለሰብ ከዚህ ቀደም በፈፀሙት ወንጀል የእድሜ ልክና የ20 ዓመት የእስር ቅጣት ተወስኖባቸዉ በሶዶ ማረሚያ ተቋም በእርምት ላይ የነበሩ ሲሆኑ ከሌሎች ሁለት ግብራበሮቻቸዉ ጋር በመሆን በድብቅ ወደ ማረሚያ ተቋም ባስገቡት ቦንብ በጥበቃ ፖሊሶች ላይ ወርዉረዉ በማፈንዳት ጥቃት አድርሰዉ ለማምለጥ ሙከራ በማድረጋቸዉ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ግለሰቦቹ በማረሚያ ቤት ዉስጥ ሆነዉ በፈፀሙት ወንጀል ክስ ሲመሰረትባቸዉ በነሱ ላይ ምስክር የሆኑ የህግ ታራሚዎች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ በሚል ስጋት አራቱ ታራሚዎች በሁለት ተከፍለዉ ከወላይታ ማረሚያ ወደ ሀላባና ዱራሜ ማረሚያ ተቋም መዘዋወራቸዉ ተነግሯል።

ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ያለፈዉ ታራሚ ወደ ሀላባ ማረሚያ ተቋም ከተዘዋወረ በኋላ በጥበቃ ፖሊሶች ላይ የእጅ ቦንብ ወርውሮ በማፈንዳት ከማረሚያ አምልጦ በፖሊስ ብርቱ ክትትል ታድኖ የተያዘ አደገኛ ፀባይ ያለዉ ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑ ተነግሯል።

ያመለጡት ሁለቱ ታራሚዎችን አድኖ ለመያዝ ብርቱ ክትትል እየተደረገ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.