ዜና፡- ከትግራይ ክልል የመረጃ እጥረት ቢኖርም በኢትዮጵያ በጦርነት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም 1.4 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

እንደዚ፣ በደብረ አባይ፣ ሰሜን-ምእራብ ትግራይ፣ እንደሚገኘው ክሊኒክ በትግይ ክልል ብዙ የጤና ተቋማት ተዘርፈዋል። ፎቶ፡ ድንበር የለሽ ሐኪሞች (ኤም ኤስ ኤፍ)

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13/ 2015 ዓ.ም፡- በትግይ ክልል በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ይሰጣሉ ከተባሉ ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑ የጤና ተቋማት ውጭ የመረጃ ውስንነት ቢኖርም በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር በጦርነቱ የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ቢያንስ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። 

በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልል ለሁለት አመታት የዘለቀው ጦርነት እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶች ለከፍተኛ ውድመት ዳርገዋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዛሬ እንደተናገሩት በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልል በተካሄደው ጦርነት ሁሉም የጤና ተቋማት ለጥፋት ተዳርገዋል ብለዋል። 

ሚኒስትሯ አያይዘውም በተጨማሪም በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተከሰቱ ግጭቶች የጤና ተቋማት እንደወደሙ ገልፀዋል።

“በትግራይ ክልል የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ የመረጃ ውሱንነቶች ስላሉን ተጨማሪ ማብራሪያ ያስፈልገዋል” ያሉት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ነገር ግን ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተሰበሰቡ መረጃዎችን ጨምሮ ጊዜያዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት “በኢትዮጵያ በተከሰቱ ሁሉም ግጭቶች የተጎዱ የጤና ተቋማትን ለማደስ ቢያንስ 1.4 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል” ብለዋል።

በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች በአጠቃላይ 3 ሺ 6 መቶ 66 የጤና ተቋማት መውደማቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በአማራ ክልል ከ40 ያላነሱ ሆስፒታሎች፣ 4 መቶ 52 ጤና ጣቢያዎች እና 1 ሺ 7 መቶ 28 ጤና ኬላዎች መውደማቸውን ገልፀው በአፋር ደግሞ ሁለት ሆስፒታሎች፣ 24 ጤና ጣቢያዎች እና 52 ጤና ኬላዎች ከስራ ውጭ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ዶክተር ሊያ አያይዘውም በኦሮሚያ 6 ሆስፒታሎች፣ 21 ጤና ጣቢያዎች እና 9 መቶ 78 ጤና ኬላዎች እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ 15 ጤና ጣቢያዎች እና 3 መቶ 48 ጤና ኬላዎች በግጭቶች ለጉዳት መዳረጋቸውን ገልፀዋል። 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህ አመት በግንቦት ወር ያወጣው ሪፖርት እንሚያመለክተው በምዕራብ ኦሮሚያ በኩል ብቻ 4 መቶ 26 የጤና ተቋማት መዘረፋቸውን እና በግጭት ምክንያት አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውን አረጋግጧል።

እስካሁን በአማራ ክልል ከሚገኙ 40 ሆስፒታሎች 35ቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በአፋር ክልል ከሚገኙት ሁለቱ ሆስፒታሎች አንዱ ጥገና ተደርጎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ዶ/ር ሊያ ተናግረዋለው።

ሚኒስትሯ አያይዘውም በደቡብ አፍሪካ በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ አመራሮች መካከል ጦርነት በዘላቂነት ለማቆም ስምምነት መፈረሙን አስታውሰው ይ የጤና ተቋማትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ያስችላል ብለዋል።

ድንበር የለሽ ሐኪሞች (ኤም ኤስ ኤፍ) ከታህሳስ አጋማሽ 2014 እስከ መጋቢት 2014 መጀመሪያ ድረስ በትግራይ ክልል ተገኝት ከተመለከቷቸው 106 የጤና ተቋማት መካከል 70 በመቶው የተዘረፉ እና ከ30 በመቶ በላይ ደግሞ የወደሙ እንደሆነ በመጋቢት 2014 ሪፖርት መደረጉ ይታወቃል። 

“አንዳንድ ዘረፋዎች አጋጣሚው በመጠቀም የተፈፀሙ ሊሆኑ ቢችሉም፣ በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች የጤና ተቋማት አገልግሎት እንዳይሰጡ ሆን ተብሎ የተበላሹ ይመስላ በብዙ ጤና ጣቢያዎች ለምሳሌ በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ደብረ አባይ እና ማይ ኩህሊ በቡድን የተበላሹ መሳሪያዎችን፣ በሮችና መስኮቶች የተሰባበሩ እና በየፎቅ ላይ ተበታትነው የሚገኙ የመድሀኒት እና የህሙማን ማህደር ማግኘታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ዘገያመለከተው።

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ “ያልተደናቀፈ” የሰብአዊ አቅርቦቶች አቅርቦትን በሚደነግገው የሰላም ስምምነት ምክንያት መድሃኒትን ጨምሮ ሰብአዊ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ ክልል መግባት መጀመሩን ሚኒስትሯ ገለፀዋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር መድኃኒቶችን ወደ ትግራይ እየላከ መሆኑን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

ባለፈው ወር የትግራይ ዶክተሮች በዋና ከተማይቱ መቀሌ የሚገኘው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ቁሳቁስ እጦት ምክንያጥ ሙሉ ለሙሉ አግልግሎት እንሰሚያቆምና ሊዘጋ እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር።  አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.